ስለ አምልኮ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ አምልኮ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ኑ እናምልከው እንስገድለትም በፈጠረን በያህዌ ፊት እንንበርከክ
አምላካችን ያህዌን አመስግኑት በእግሩ መርገጫ ስገዱ፡፡ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡
«ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤አንተ ሁሉንም ነገር ስለፈጠርህ፥በፈቃድህ ስለፈጠርሃቸውና እንደዚያም ሆነው ስለተገኙ ክብር፥ሞገስ፥ኅይልም ልትቀበል ይገባሃል።» ይሉ ነበር።
ለስሙ የሚገባውን ክብር ለያህዌ ስጡ በቅድስናው ውበት ለያህዌ ስገዱ
ክብርን በተሞላ ቅድስና ለያህዌ ስገዱ ምድር ሁሉ በፊቱ፤ ተንቀጥቀጡ፡፡
ክብርህን በላይ በሰማያት የምትገልጥ አንተ ጌታችን ያህዌ፣ ስምህ በምድር ሁሉ ምንኛ ገናና ነው፡፡
እነርሱም በታላቅ ድምፅ፥«የታረደው በግ ኀይልና ባለጠግነት፥ጥበብና ብርታት፥ምስጋና እና ክብር ሊቀበል ይገባዋል።» አሉ።
በሰማይና በምድር፥ከምድር በታች እንዲሁም በባሕር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ ፥«ምስጋና፥ክብር፥ውዳሴ፥የመግዛትም ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና ለበጉ ይሁን።» ሲሉ ሰማሁ፤
ያህዌ ምስጋናው ታላቅ ነው ታላቅነቱም አይመረመርም፡፡
አንዱም አንደኛውን በመጥራት፣ "ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር! ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች" እያለ ይጮኽ ነበር።
ታማኝነትህ ከሕይወት ይበልጣልና ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል፡፡
ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ሰጡ፤መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤በቅድስናውም ክብር ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
ከፀሐይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ የያህዌ ስም ይመስገን፡፡