ስለ አምልኮ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ አምልኮ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዮሐንስ 4:24

እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባል።»

ለስሙ የሚገባውን ክብር ለያህዌ ስጡ በቅድስናው ውበት ለያህዌ ስገዱ

03 ሮሜ 12:1

ስለዚህም ወንድሞች ሆይ ሥጋችሁን ህያው መስዋዕት፥ቅዱስ፥ ለእግዚአብሔር የሚገባ አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ምህረት እለምናችኋለሁ፥ ያም ተገቢ የሆነ አገልግሎታችሁ ነው።

«ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤አንተ ሁሉንም ነገር ስለፈጠርህ፥በፈቃድህ ስለፈጠርሃቸውና እንደዚያም ሆነው ስለተገኙ ክብር፥ሞገስ፥ኅይልም ልትቀበል ይገባሃል።» ይሉ ነበር።

ያህዌን በደስታ አገልግሉት፡፡ በደስታ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ

ኑ እናምልከው እንስገድለትም በፈጠረን በያህዌ ፊት እንንበርከክ

ክብርን በተሞላ ቅድስና ለያህዌ ስገዱ ምድር ሁሉ በፊቱ፤ ተንቀጥቀጡ፡፡

08 ዕብራዊያን 12:28

ስለዚህ፣ ሊናወጥ የማይችል መንግሥት ስለተቀብልን አምላካችንን እናመስግነው፣ ደግሞም እግዚአብሔርን ተቀባይነት ባለው በአክብሮትና በፍርሃት እናምልከው፣

09 ዘጸአት 34:14

ስሜ ‘ቀናተኛ’ የሆነ እኔ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና ሌላ አምላክ አታምልክ።

አምላካችን ያህዌን አመስግኑት በእግሩ መርገጫ ስገዱ፡፡ እርሱ ቅዱስ ነው፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች