ስለ ቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ቤት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኢያሱ 24:15

እግዚአብሔርንም ማምለክ ክፉ መስሎ ቢታያችሁ፥ እባቶቻችሁ በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ሳሉ ያመለኩአቸውን አማልክት ወይም በምድራቸው ያላችሁባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደ ሆነ፥ የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤተ ሰቦቼ ግን እግዚአብሔርን እናመካለን።

ያህዌ ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ ያህዌ ከተማን ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል፡፡

03 ምሳሌ 24:3-4

ቤት በጥበብ ይሰራል፣ በማስተዋልም ይጸናል፡፡ በእውቀትም ውድና ባማሩ እቃዎች ክፍሎቹ ይሞላሉ፡፡

04 ምሳሌ 14:1

ጥበበኛ ሴት ቤቷን ትሰራለች፣ ሞኝ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች፡፡

እነርሱም፣ “በጌታ ኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት።

06 ኦሪት ዘዳግም 6:9

በቤታችሁም መቃኖች በደጃፋችሁም በሮች ላይ ጻፉት።

07 ምሳሌ 12:7

ክፉ ሰዎች ይገለበጣሉ፣ አይገኙምም፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ቤት ግን ጸንቶ ይቆማል፡፡

08 ምሳሌ 15:6

ጽድቅን በሚያደርጉ ሰዎች ቤት ብዙ ሀብት አለ፣ ክፉ ሰዎች የሚያገኙት ገቢ ግን መከራ ያመጣባቸዋል፡፡

በቤትህ ውስጥ ሚስትህ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች ልጆችህም በማእድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ተክል ይሆናሉ፡

10 ምሳሌ 31:27

የቤተሰቦቿን መንገዶች ትመለከታለች፣ የስንፍናንም እንጀራ አትበላም፡፡

11 1 ጢሞቴዎስ 5:8

ነገር ግን ማንም ለዘመዶቹ የሚያስፈልጋቸውን የማይሰጥ፣ ይልቁንም ለገዛ ቤተሰቡ የማያስብ እምነትን የካደ ከማያምን ሰው ይልቅ የከፋ ነው፡፡

ነቀፋ በሌለበት መንገድ እሄዳለሁ አንተ ወደ እኔ የምትመጣው መቼ ነው? በቤቴ ውስጥ ያለ ነቀፋ እመላለሳለሁ፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች