ስለ ፍቅርና መከባበር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ፍቅርና መከባበር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኤፌሶን 5:33

ግን ከእናንተ እያንዳንዱ ደግሞ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ መውደድ ይገባዋል፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር።

02 ኤፌሶን 5:25

ባሎች ሆይ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ስለ እርስዋም ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ፥ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ።

03 1ኛ ጴጥሮስ 3:1-2

ሚስቶች ሆይ፤ እናንተም እንደዚሁ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ አንዳንድ ለቃሉ የማይታዘዙ ቢኖሩ እንኳ፣ ሚስቶቻቸው ቃል ሳይናገሩ በመልካም አኗኗራቸው ሊማርኳቸው ይችላሉ፤ ይህም የሚሆነው ለእነርሱ ያላችሁን አክብሮት በንጹሕ አኗኗራችሁ ሲመለከቱ ነው።

04 ቆላስይስ 3:19

ባሎች ሆይ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው።

05 1ኛ ቆሮንቶስ 13:4-5

ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። ፍቅር አይመቀኝም ደግሞም አይመካም። አይታበይም ወይም ትህትና የጎደለው አይደለም። ራስ ወዳድ አይደለም። በቀላሉ አይበሳጭም፤ወይም በደልን አይቆጥርም።

06 1ኛ ጴጥሮስ 3:7

እንዲሁም ባሎች ሆይ፤ ሚስቶቻችሁ ደካማ አጋር መሆናቸውን ዐውቃችሁ፣ የሕይወትን ጸጋ ከእናንተ ጋር አብረው የሚካፈሉ መሆናቸውንም ተገንዝባችሁ አብራችኋቸው ኑሩ። ጸሎታችሁ እንዳይከለከል ይህን አድርጉ።

07 ሮሜ 12:10

እውነተኛ የወንድማማች ፍቅር ይኑራችሁ፤ እርስ በእርሳችሁ ተከባበሩ።

ተዛማጅ ርዕሶች