ስለ ኄር ሚስት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ኄር ሚስት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ችሎታ ያላትን ሴት ማን ሊያገኛት ይችላል? የእርሷ ዋጋ ከእንቁ የበለጠ ነው፡፡
ጥንካሬንና ክብርን ተላብሳለች፣ ወደፊት የሚመጣውን ጊዜ እያሰበች ትስቃለች፡፡ አፏን በጥበብ ትከፍታለች፣ የደግነት ሕግም በምላሷ ላይ አለ፡፡
ቁንጅና አሳሳች ነው፣ ውበትም ጠፊ ነው፣ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች፡፡
መልካም ሴት ለበሏ ዘውድ ናት፣ አሳፋሪ ሴት ግን አጥንቱን እንደሚያበሰብስ በሽታ ናት፡፡
ሚስትን ያገኘ መልካምን ነገር አግኝቷል፣ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን አግኝቷል፡፡
የባሏ ልብ በእርሷ ይተማመናል፣ ድሃም አይሆንም፡፡
የቤተሰቦቿን መንገዶች ትመለከታለች፣ የስንፍናንም እንጀራ አትበላም፡፡ ልጆቿም አድገው የተባረክሽ ነሽ ይሏታል፤ ባለቤቷም እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል፣
ቤትና ሐብት ከወላጆች ይወረሳል፣ ጠንቃቃ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ናት፡፡
ጥበበኛ ሴት ቤቷን ትሰራለች፣ ሞኝ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች፡፡
ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን ይኸውም ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በመንቆጥቆጥ ወይም ጌጠኛ ልብስ በመልበስ አይሁን፤ ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምንጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን።
እጇን ለድሆች ትዘረጋለች፤ ለተቸገሩትም እጆቿን ትዘረጋለች፡፡
ወጣት ሴቶችን በአስተሳሰባቸው ሚዛናዊ እንዲሆኑ እንዲያሳስቧቸው፣ የገዛ ባሎቻቸውና ልጆቻቸውን የሚወዱ፣ ጠንቃቃ እንዲሆኑ እንዲያበርቷቷቸው፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ ንፁህ፣ መልካም የቤት አስተዳዳሪና፣ ለባሎቻቸውም የሚታዘዙ ይሁኑ።