ስለ ልጆችን ማሳደግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ልጆችን ማሳደግ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እናንተም አባቶች ሆይ፤ ልጆቻችሁን አታስቆጡአቸው፤ ይልቁንስ በጌታ ሥርዓትና ምክር አሳድጓቸው።
ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፣ በሸመገለም ጊዜ ከነገርከው መንገድ ፈቀቅ አይልም፡፡
እኔም ዛሬ እናንተን የማዝዘው ቃል በልባችሁ ይሁን፤ በቤታችሁም ስትቀመጡ፥ በመንገድም ስትሄዱ፥ ስትተኙም፥ ስትነሡም፥ ልጆቻችሁን አስተምሩአቸው።
እነሆ ልጆች የያህዌ ስጦታ ናቸው የማሕፀንም ፍሬ የእርሱ ችሮታ ነው፡፡
ልጅህን ቅጣው እረፍትም ይሰጥሃል፤ ለሕይወትህም ደስታን ያመጣል፡፡
ልጁን የማይቀጣ ይጠላዋል፣ ልጁን የሚወድ ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል፡፡
ሞኝነት በሕጻን ልብ ላይ ታስሯል፣ የስርዓት በትር ግን ከእርሱ ያርቀዋል፡፡
እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም ስለ እግዚአብሔር ኃይል ስላከናወናቸውም ታላላቅ ሥራዎችና ስላደረጋቸው ድንቅ ነገሮች ለተከታዩ ትውልድ እንገራለን፡፡ ለያዕቆብ ሥርዐትን መሠረተ ለእስራኤልም ሕግን ደነገገ፡፡ ይህንንም ለሚቀጥለው ትውልድ እንዲያስተምሩ አባቶቻችንን አዘዘ፡፡ ይህም የሚመጣው ትውልድ ሥርዐቱን እንዲያውቅ እነርሱም በተራቸው ለልጆቻቸው ገና ለሚወለዱትም እንዲነግሩ ነው፡፡
ተስፋ ሳለ ልጅህን ስርዓት አስይዘው፣ ሞቱንም እየተመኘህ ዝም ብለህ አትየው፡፡
ከሕፃንነትህ ጀምሮ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ስለሚገኘው መዳን ጥበብ ሊሰጡህ ስለሚችሉት ቅዱሳት መጻሕፍት አውቀሃል፡፡
ወጣት እንኳ ባህርዩ ንጹህና ቅን መሆኑ በስራው ይታወቃል፡፡
አባቶች ሆይ፥ልጆቻችሁ ተስፋ እንዳይቆርጡ አታስመርሩአቸው።