ስለ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ልጆችን ማሳደግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ልጆችን ማሳደግ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፣ በሸመገለም ጊዜ ከነገርከው መንገድ ፈቀቅ አይልም፡፡
እኔም ዛሬ እናንተን የማዝዘው ቃል በልባችሁ ይሁን፤ በቤታችሁም ስትቀመጡ፥ በመንገድም ስትሄዱ፥ ስትተኙም፥ ስትነሡም፥ ልጆቻችሁን አስተምሩአቸው።
እናንተም አባቶች ሆይ፤ ልጆቻችሁን አታስቆጡአቸው፤ ይልቁንስ በጌታ ሥርዓትና ምክር አሳድጓቸው።
እኛም ከልጆቻቸው አንደብቀውም ስለ እግዚአብሔር ኃይል ስላከናወናቸውም ታላላቅ ሥራዎችና ስላደረጋቸው ድንቅ ነገሮች ለተከታዩ ትውልድ እንገራለን፡፡
ልጅህን ቅጣው እረፍትም ይሰጥሃል፤ ለሕይወትህም ደስታን ያመጣል፡፡
ሞኝነት በሕጻን ልብ ላይ ታስሯል፣ የስርዓት በትር ግን ከእርሱ ያርቀዋል፡፡
ልጁን የማይቀጣ ይጠላዋል፣ ልጁን የሚወድ ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል፡፡
ያለህንም እውነተኛ እምነት አስባለሁ፣ ይህም እምነት አስቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፣ በአንተም እንዳለ ተረድቼአለሁ፡፡
ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ምክር ስማ፣ የእናትህንም ሕግ አትተው፤ ለራስህ የሞገስ አክሊል፣ ለአንገትህ ደግሞ ውበት የሚሰጥ ጌጥ ይሆኑልሃል፡፡
ልጆችሽም ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፣ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል።
ዓይኖቻችሁ ያዩትን ነገር እንዳትረሱ በሕይወታችሁም ዘመን ሁሉ ከልባችሁ እንዳይጠፋ ብቻ አስታውሉ፤በጥንቃቄም ራሳችሁን ጠብቁ። እግዚአብሔር፦ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ በምድርም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩ ዘንድ ልጆቻቸውንም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን አሰማቸዋለሁ ብሎ እንደተናገረኝ፥
ልጆቼ በእውነት መንገድ እየሄዱ እንደሆነ ከመስማት የበለጠ ደስታ የለኝም።