ስለ ባልና ሚስት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ባልና ሚስት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኤፌሶን 5:25

ባሎች ሆይ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ስለ እርስዋም ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ፥ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ።

02 1ኛ ጴጥሮስ 3:7

እንዲሁም ባሎች ሆይ፤ ሚስቶቻችሁ ደካማ አጋር መሆናቸውን ዐውቃችሁ፣ የሕይወትን ጸጋ ከእናንተ ጋር አብረው የሚካፈሉ መሆናቸውንም ተገንዝባችሁ አብራችኋቸው ኑሩ። ጸሎታችሁ እንዳይከለከል ይህን አድርጉ።

03 ኤፌሶን 5:33

ግን ከእናንተ እያንዳንዱ ደግሞ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ መውደድ ይገባዋል፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር።

04 ቆላስይስ 3:18-19

ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ታዘዙ። ባሎች ሆይ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው።

05 1ኛ ቆሮንቶስ 7:3

ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፤ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ የሚገባትን ታድርግ።

06 1ኛ ጴጥሮስ 3:1

ሚስቶች ሆይ፤ እናንተም እንደዚሁ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ አንዳንድ ለቃሉ የማይታዘዙ ቢኖሩ እንኳ፣ ሚስቶቻቸው ቃል ሳይናገሩ በመልካም አኗኗራቸው ሊማርኳቸው ይችላሉ፤

07 ኤፌሶን 5:28

ባሎች የገዛ ሥጋቸውን እንደሚወዱ ሚስቶቻቸውን መውደድ ይገባቸዋል። ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል።

ተዛማጅ ርዕሶች