ስለ ጋብቻ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ጋብቻ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።

02 ኤፌሶን 5:31

ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ከሚስቱም ጋር አንድ ይሆናል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።

03 ዕብራዊያን 13:4

ጋብቻ በሁሉም ዘንድ የተከበረ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በሴሰኞችና በአመንዝራዎች ላይ ይፈርድባቸዋል።

04 ማርቆስ 10:9

እንግዲህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው አላቸው፡፡

05 ምሳሌ 18:22

ሚስትን ያገኘ መልካምን ነገር አግኝቷል፣ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን አግኝቷል፡፡

06 1ኛ ቆሮንቶስ 13:4-7

ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። ፍቅር አይመቀኝም ደግሞም አይመካም። አይታበይም ወይም ትህትና የጎደለው አይደለም። ራስ ወዳድ አይደለም። በቀላሉ አይበሳጭም፤ወይም በደልን አይቆጥርም። ፍቅር በአመጽ ደስ አይሰኝም፣በእውነት ግን ደስ ይለዋል። ፍቅር ሁሉን ይታገሳል፤ሁሉን ያምናል፤በሁሉም ድፍረት አለው በሁሉ ይጸናል።

07 ቆላስይስ 3:14

በዚህ ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነው ፍቅር ይኑራችሁ።

በልብህ ላይ እንደ ማኅተም አስቀምጠኝ፥ እንደ ማኅተም በክንድህ ላይ፥ ፍቅር እንደ ሞት ብርቱ ነውና። የታማኝነቷም ጠንካራ ስሜት እንደ ሲዖል ጨካኝ ነው፤ ነበልባሏ ይነዳል፤ የምትንቦገቦግ ነበልባል ናት፥ ነበልባሏ ከሌላ ከየትኛውም እሳት ይልቅ የጋለ ነው። የማዕበል ውሃ ፍቅርን ለማጥፋት አይችልም፥ ጎርፍም ሊያሰጥመው አይችልም። ሰው በቤቱ ያለውን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ብሎ ቢሰጥ ስጦታው ፈጽሞ ይናቃል። የወጣቷ ወንድሞች እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ፥

09 መክብብ 4:9-10

ከአንድ ሰው ይልቅ ሁለቱ የተሻለ ሥራ ይሠራሉ፤ በጋራ ለሥራቸው የተሻለ ገቢ ማግኘት ይችላሉ። አንደኛው ቢወድቅ ሌላኛው ጓደኛውን ሊያነሣው ይችላልና። በመሆኑም በወደቀ ጊዜ የሚያነሣው ካልኖረ ብቸኛውን ሰው ሀዘን ይከተለዋል።

10 ምሳሌ 5:18-19

ምንጭህ የተባረከ ይሁን፣ በወጣትነት ሚስትህም ደስ ይበልህ፡፡ ምክንያቱም እርሷ በፍቅር እንደተሞላች ዋላ፣ ግርማ ሞገስ እንዳላትም ሚዳቋ ናት፡፡ ጡቷም ሁልጊዜ ያስደስትህ፣ ሁልጊዜም በፍቅሯ ተማረክ፡፡

11 1ኛ ቆሮንቶስ 7:2-3

ነገር ግን ስለ ዝሙት ፈተና ምክንያት እንዳይሆን እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሚስት ይኑረው፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ሴት የራስዋ ባል ይኑራት። ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፤ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ የሚገባትን ታድርግ።

በመንፈሱ ክፋይ እግዚአብሔር አንድ አላደረጋቸውምን? እርሱ አንድ ያደረጋችሁ ለመንድነው? ምክንያቱም ለእግዚአብሔር የሚሆን መሥዋዕት ስለፈለገ ነው። ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ ከወጣትነት ሚስታችሁ ጋር ያላችሁንም ታማኝነት አታጉድሉ።

ተዛማጅ ርዕሶች