ስለ መደገፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ መደገፍ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
የከበድህን ነገር በያህዌ ላይ ጣል እርሱ ደግፎ ይይዝሃል፤ የጻድቁን መናወጥ ከቶ አይፈቅድም፡፡
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፣ አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፣ እረዳህማለሁ፣ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
እነሆ እግዚአብሔር ረዳቴ ነው ጌታም ደግፎ ይይዘኛል፡፡
እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፣ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻለሁ እኔም አነሣለሁ፤ እኔ እሸከማለሁ እኔም አድናለሁ።
የማዳን ጋሻህን ሰጠኸኝ፤ ቀኝ እጅህ ደግፎኛል፤ ሞገስህም ታላቅ አድርጐኛል፡፡
በሰላም እተኛለሁ፤ እንቀላፋለሁ ያህዌ ስለ ጠበቀኝ ከእንቅልፌ ተነሣሁ፡፡
እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፣ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፣ አይደክሙም።
ያህዌ የሚንገዳገዱትን ሁሉ ይደግፋል የወደቁትንም ሁሉ ያነሣል፡፡
ዘላለማዊ አምላክ መኖርያህ ነው፤ የዘላለም ክንዶቹም ከበታችህ ናቸው፤ እርሱን አጥፋው! በማለት፤ ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል።
ያህዌ በእጁ ደግፎ ስለሚይዘው ቢሰናከል እንኳ አይወድቅም፡፡
በሕይወት እኖር ዘንድ በቃልህ ደግፈኝ ተስፋዬም መና ቀርቶ አልፈር፡፡
ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት የተነሳ ነው፥ የምሕረቱ ሥራዎች አያልቁምና። የምሕረቱ ሥራዎች ማለዳ ማለዳ አዲስ ናችው፤ ታማኝነትህ ምንኛ ታላቅ ነው!
እኔ፣ «እግሬን አዳለጠኝ» ባልሁ ጊዜ ያህዌ ሆይ፣ ምሕረትህ ደግፎ ያዘኝ፡፡
ለአርባ አመታት በበረሃ ተጠነቀቅክላቸው፡፡ በነዚያ ጊዜያት ሁሉ፣ የአንዳች ነገር ጉድለት አልነበረባቸውም፡፡ ልብሳቸው አላረጀም፣ እግሮቻቸው አላበጡም፡፡
እግርህ እንዲንሸራተት አይፈቅድም አንተን የሚጠብቅህም አይተኛም፡፡