ስለ ፈውስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ፈውስ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እግዚአብሔር ሆይ፣ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ! አድነኝ እኔም እድናለሁ። አንተ የምስጋናዬ ዝማሬ ነህና።
ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን አመሰግኚ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፡፡ ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር ይላል ደዌሽንም ሁሉ ይፈውሳል፡፡
እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፣ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፣ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
እንዲህ አለ፤ “የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፥ ትክክለኛ የሆነውንም በፊቱ ብታደርጉ፣ ትእዛዛቱንም ብታስተውሉና ሕግጋቱን ሁሉ ብትጠብቁ፣ ግብፃውያን ላይ ካመጣኋቸው በሽታዎች አንዱንም በእናንተ ላይ አላመጣም፤ እኔ ፈዋሻችሁ እግዚአብሔር ነኝና።”
ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል ቁስላቸውንም ይጠግናል፡፡
ያህዌ ሆይ፣ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ጮኽሁ አንተም ፈውሰኸኝ፡፡
የእምነት ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሳል፤ ጌታም ያስነሣዋል። ኃጢአት አድርጎ ከሆነም እግዚአብሔር ይቅር ይለዋል።
ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን ፈውስ በክንፎቹ የያዘ የጽድቅ ፀሐይ ይወጣላቸዋል። እናንተም ከጋጥ እንደተለቀቁ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ።
ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።
ታሞ በተኛበት አልጋ ያህዌ ይንከባከበዋል በበሽታውም ጊዜ መኝታውን ያነጥፍለታል፡፡
ኢየሱስ በምኵራቦቻቸው ውስጥ እያስተማረ፣ የመንግሥትን ወንጌልም እየሰበከና በሕዝቡ መካከል ያሉ በሁሉም የደዌና የበሽታ ዐይነት የሚሠቃዩትን እየፈወሰ በመላው ገሊላ ተዘዋወረ፡፡
በራስህ አስተያየት ጥበበኛ አትሁን፤ እግዚብሔርን ፍራ፣ ከክፉም ራቅ፡፡ ይህም ለስጋህ ፈውስ፣ ለሰውነትህም መታደስ ይሆንልሃል፡፡
ኑ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ። እርሱ ገነጣጥሎናል፥ ነገር ግን እርሱ ይፈውሰናል፤ እርሱ አቁስሎናል፥ ነገር ግን እርሱ ቁስላችንን አስሮ ይጠግናል።