ስለ ሸለቆው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ሸለቆው የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

በጨለማው የሞት ሸለቆ ውስጥ እንኳ ባልፍ አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ ጉዳት ይደርስብኛል ብዬ አልፈራም፡፡

ያህዌ እረኛዬ ነው፤ ምንም አላጣም፡፡ በለመለመ መስክ ያሳድረኛል ፀጥ ባለ ውሃ ዘንድ ይመራኛል፡፡ ነፍሴን ይመልሳታል፤ ያድሳታል፡፡ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ ይመራኛል፡፡

03 ኢሳይያስ 43:2

በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፣ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።

እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኃይላችን፣ በመከራም ቀን ረዳታችን ነው፡፡ ስለዚህ ምድር ብትናወጥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ፣ አንፈራም፡፡

በልቅሶ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ የሚጠጡት የምንጭ ውሃ ያገኛሉ የበልግም ዝናብ ይሞላዋል፡፡

በጠላቶቼ ፊት ለፊት በፊቴ ገበታ አዘጋጀህልኝ ራሴን በዘይት ቀባህ ጽዋዬ ሞልቶ ተርፏል፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች