ስለ ሕመም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ሕመም የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ያዕቆብ 5:14-15

በእናንተ መካከል የታመመ አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት እየቀቡ ይጸልዩለት፤ የእምነት ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሳል፤ ጌታም ያስነሣዋል። ኃጢአት አድርጎ ከሆነም እግዚአብሔር ይቅር ይለዋል።

ታሞ በተኛበት አልጋ ያህዌ ይንከባከበዋል በበሽታውም ጊዜ መኝታውን ያነጥፍለታል፡፡

03 የማቴዎስ 8:16-17

በመሸ ጊዜ፣ ሕዝቡ አጋንንት የያዙአቸውን ብዙዎችን ወደ ኢየሱስ አመጡ፣ እርሱም በቃሉ፣ መናፍስቱን አስወጣቸው፤ ታመው የነበሩትንም ሁሉ ፈወሳቸው። በዚህ ዐይነት፣ በነቢዩ ኢሳይያስ፣ “እርሱ ሕመማችንን ተቀበለ ደዌዎቻችንን ተሸከመ” ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ።

04 ኢሳይያስ 53:4

በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።

ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌን አመሰግኚ ውለታውንም ሁሉ አትርሺ፡፡ ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር ይላል ደዌሽንም ሁሉ ይፈውሳል፡፡

ጌታ ሆይ፣ የጥልቅ ልቤን ናፍቆት አንተ ታውቃለህ መቃተቴም ከአንተ የተሰወረ አይደለም፡፡

07 ማርቆስ 2:17

ይህን ሲሰማ፣ "ሕሙማን እንጅ ጤናሞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም" ፤ እኔ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች