ስለ መከራ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ መከራ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ይህ ጊዜያዊ፣ ቀላል መከራችን መለኪያ ለሌለው፥ ለላቀው ዘላለማዊ ክብር የሚያዘጋጀን ነው።
የጻድቅ መከራው ብዙ ነው ያህዌ ግን ከሁሉም ያድነዋል፡፡
03 ሮሜ 8:28
እግዚአብሔርን ለሚወዱት፥ በዓላማው ለተጠሩት ለእነርሱ ሁሉን ነገር አጣጥሞ ለመልካም እንደሚሠራላቸው እናውቃለን።
በሁሉ መንገድ መከራን እንቀበላለን፥ሆኖም በዚያ አንዋጥም። እናመነታለን ነገር ግን ተስፋ በማጣት አንረበሽም። ቢሆንም ግን ተረስተን አንቀርም።
ሥርዐትህን እማር ዘንድ በመከራ ውስጥ ማለፌ መልካም ሆነልኝ፡፡
የተስፋ ቃልህ ሕያው አድርጐኛልና ይህ በመከራዬ መጽናኛዬ ሆነ፡፡
ያህዌ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል፡፡
ያህዌ ለተጨቆኑት ዐምባ ነው፡፡ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል፡፡
አንዳች ጉዳት ሳይደርስብኝ መንገድ ስቼ ሄድሁ አሁን ግን ቃልህን እጠብቃለሁ፡፡
ሐዘንን ቢያመጣም እንኳን ከታላቁ የኪዳኑ ታማኝነት በሚሆን ርኅራኄ ይራራል። ምክንያቱም ከልቡ አይጨቁንም፥ወይንም የሰዎችን ልጆች አያሰቃይም።
11 ኢዮብ 5:17
እነሆ፥ እግዚአብሔር የሚያርመው ሰው ምስጉን ነው፤ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን አምላክንተግሣጽ አትናቅ።
12 ትንቢተ ናሆም 1:7
ያህዌ መልካም ነው፤ በመከራ ጊዜም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑበት ታማኝ ነው፡፡