ስለ ደኅንነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ደኅንነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ሮሜ 10:9

ስለዚህም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ።

በሌላ በማንም ድነት የለም፤ ልንድንበት የሚገባ በሰዎች መካከል የተሰጠ ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።”

03 ሮሜ 10:10

ምክንያቱም ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል በአፉ መስክሮ ደግሞ ይድናል።

04 ዮሐንስ 3:17

እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ላይ ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው።

05 ቲቶ 2:11

ሰዎችን ሁሉ ሊያድን የሚችለው የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጧል፡፡

06 2ኛ ቆሮንቶስ 6:2

ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ብሏልና "በምቹ ጊዜ ሰማሁህ በድነትም ቀን ረዳሁህ።" ልብ በሉ፥ ምቹ ጊዜም ሆነ የድነት ቀን አሁን ነው።

07 1 ጢሞቴዎስ 2:4

እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ሁሉ ወደ ማውቅ እንዲደርሱ ይፈልጋልና፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች