ስለ ዘላለማዊ ሕይወት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ዘላለማዊ ሕይወት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዮሐንስ 3:16

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፤

02 ዮሐንስ 10:28

የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለው፤ ፈጽሞም አይጠፉም፤ ነጥቆ ከእጄ የሚያወጣቸው ማንም የለም።

03 ዮሐንስ 17:3

ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተን፣ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያውቁ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው፡፡

04 1ኛ ዬሐንስ 5:11-12

ምስክሩም ይህ ነው ፣እግዚአብሔር የዘላለምን ህይወት እንደሰጥንና፣ይህም ህይወት በልጁ መሆኑ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።

05 ዮሐንስ 6:47

እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፡፡

06 ሮሜ 6:23

የኃጢአት ደሞዝ ሞት ሲሆን የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የዘላለም ሕይወት ነው።

07 1ኛ ዬሐንስ 5:13

በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ፣የዘላለም ህይወት እንዳላችሁ እንድታውቁ ፣እነዚህን ነገሮች እጽፍላችኋለሁ።

08 ቲቶ 1:2

የማይዋሽ እግዚአብሔር፣ በተረጋገጠ ዘላለማዊ ሕይወት ከዘመናት በፊት ተስፋን ሰጠ፣

ተዛማጅ ርዕሶች