ስለ መመስከርና ማመን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ መመስከርና ማመን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ሮሜ 10:9-10
ስለዚህም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ። ምክንያቱም ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል በአፉ መስክሮ ደግሞ ይድናል።
02 ሮሜ 10:13
የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።
03 የማቴዎስ 10:32
ስለዚህ በሰዎች ፊት ለሚመሰክርልኝ፣ እኔም በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፡፡
04 1ኛ ዬሐንስ 4:15
ማንም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ቢቀበል፣ እግዚአብሔር በርሱ ይኖራል ፤እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል፡፡
እነርሱም፣ “በጌታ ኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት።
06 ሮሜ 10:11
ምክንያቱም መጽሀፍ እንደሚል «በእርሱ የሚያምን አያፍርም» ።