ስለ ዳግመኛ መወለድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ዳግመኛ መወለድ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ኢየሱስ፣ «እውነት እልሃለሁ፣ ሰው ዳግም ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም» ብሎ መለሰለት።
ኢየሱስ መልሶ፣ «እውነት፣ እውነት፣ እልሃለሁ፣ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
'ዳግም መወለድ አለባችሁ' ስላልሁህ አትደነቅ፤
ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤ ነገር ግን በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው።
ከምህረቱ የተነሳ፣ በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታድስ አዳነን እንጂ፣ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ምክንያት አይደለም።
ስለሆነም ማንም በክርስቶስ ውስጥ ቢሆን እርሱ አዲስ ፍጥረት ነው። አሮጌ ነገሮች አልፈዋል። ተመልከቱ፥ ሁሉ አዲስ ሆኗል።
ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የመሆንን መብት ሰጣቸው፡፡ እነርሱም ከደምና ከሥጋ ወይም ከሰው ፈቃድ አልተወለዱም፤ ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፡፡
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በመነሣቱ ምክንያት ላገኘነው ርስት ዋስትና እንዲሆነን በታላቅ ምሕረቱ አዲስ ልደትን ሰጠን፤
ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዷል።አባት የሆነውን የሚወድ ሁሉ፣ከርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።
በፍጥረታቱ መካከል እንደ በኵራት እንድንሆን እግዚአብሔር በእውነት ቃል ሕይወት ሊሰጠን ወደደ።
አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።
ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።
እንግዲህ ከሞቱ ጋር ለመተባበር በጥምቀት አማካይነት ከእርሱ ጋር ተቀብረናል። ይህም የሆነው ልክ ክርስቶስ በአብ ኃይል ከሙታን እንደ ተነሣ እኛ ደግሞ በታደሰ ሕይወት እንድንመላለስ ነው።
እርሱ ፃድቅ እንደሆነ ካወቃችሁ ፣ፅድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከርሱ እንደተወለደ ታውቃላችሁ፡፡