ስለ ጠባቡ በር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ጠባቡ በር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
በጠባቡ በር ግቡ፣ ምክንያቱም ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ሰፊ፣ የሚሄዱበትም ብዙዎች ናቸው፡፡ በሩ ጠባብ፣ ወደ ሕይወት የሚወስደውም መንገድ ቀጭን ስለ ሆነ፣ የሚያገኙት ጥቂቶች ናቸው፡፡
"በጠባብዋ በር ለመግባት ታገሉ፣ ብዙዎች በዚህች በር ሊገቡ ይሞክራሉ ነገር ግን ሊገቡባት አይችሉም።
ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ «እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ፤ በእኔ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ አብ ሊመጣ አይችልም።
በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እንጂ፣" ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣" እያለ የሚጠራኝ ሁሉ፣ ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገባ አይደለም፡፡
ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፣ ፍጻሜዋ ግን ወደ ሞት ይመራል፡፡
አንድ ሰው፣ "ጌታ ሆይ፤ የሚድኑት ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸውን?" ብሎ ጠየቀው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "በጠባብዋ በር ለመግባት ታገሉ፣ ብዙዎች በዚህች በር ሊገቡ ይሞክራሉ ነገር ግን ሊገቡባት አይችሉም።
በሩ እኔ ነኝ። ማንም በእኔ በኩል ቢገባ፣ ይድናል፤ ይገባል፣ ይወጣልም፤ መሰማሪያም ያገኛል።
በሌላ በማንም ድነት የለም፤ ልንድንበት የሚገባ በሰዎች መካከል የተሰጠ ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።”
ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር፣ ራሱን መካድ፣ የራሱን መስቀል መሸከምና እኔን መከተል አለበት፡፡
ለሁሉም እንዲህ አላቸው፤ "እኔን መከተል የሚፈልግ ራሱን ይካድ ዕለት ዕለትም መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ።
በዚያ ቀን ብዙዎች፣ "ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣ በስምህ ትንቢት ተናግረን አልነበረም እንዴ፣ በስምህ አጋንንት አስወጥተን አልነበረም እንዴ፣ በስምህስ ብዙ ታላላቅ ነገሮችን አድርገን አልነበረም እንዴ?" ይሉኛል፡፡ እኔም፣ “እናንት ክፉ አድራጊዎች፣ የት ዐውቃችሁና ነው? ከእኔ ራቁ ብዬ በግልጽ እነግራቸዋለሁ”
ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ፣ ቅድስናንም ተከታተሉ፣ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ሊያይ አይችልም።
ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማጽናት ትጉ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም፤
ኢየሱስም እንደ ገና እንዲህ አላቸው፤ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ የበጎች በር እኔ ነኝ።