ስለ ከሞት ወደ ሕይወት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ከሞት ወደ ሕይወት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዮሐንስ 5:24

እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ አይፈረድበትም።

02 ኤፌሶን 2:4-5

ነገር ግን እግዚአብሔር ምሕረት በማድረግ ባለጠጋ ስለሆነ፥ ከወደደን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ በበደላችን ሙታን በነበርንበት ጊዜ እንኳ ከክርስቶስ ጋር አዲስ ሕይወት ሰጠን፤የዳናችሁትም በጸጋ ነው፤

03 ቆላስይስ 2:13

እናንተም በበደላችሁና በሥጋችሁ ባለመገረዝ ሙታን ሳላችሁ፤ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ሕያዋን አድርጎ መተላለፋችንንም ሁሉ ይቅር ብሎአል።

04 1ኛ ዬሐንስ 3:14

ወንድሞችን ስለምንወድ ፣ከሞት ወደ ህይወት እንደተሻገርን እናውቃለን። ፍቅር የሌለው በሞት ውስጥ ይኖራል፡፡

05 ሮሜ 6:13

ከሙታን ሕያው እንደመሆናችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ የሰውነት ክፍሎቻችሁን የአመጻ መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ። የሰውነት ክፍሎቻችሁን ለእግዚአብሔር የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ አቅርቡ።

06 ዮሐንስ 11:25-26

ኢየሱስ፣ “እኔ ትንሣኤና ሕይወት ነኝ፣ በእኔ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፡፡ በእኔ የሚኖርና የሚያምንብኝ ሁሉ ፈጽሞ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽን?” አላት፡፡

07 ሮሜ 6:4

እንግዲህ ከሞቱ ጋር ለመተባበር በጥምቀት አማካይነት ከእርሱ ጋር ተቀብረናል። ይህም የሆነው ልክ ክርስቶስ በአብ ኃይል ከሙታን እንደ ተነሣ እኛ ደግሞ በታደሰ ሕይወት እንድንመላለስ ነው።

08 ገላቲያ 2:20

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።

09 1ኛ ጴጥሮስ 2:24

ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።

10 ኤፌሶን 2:1

እንግዲህ እናንተ ከበደላችሁና ከሓጢአታችሁ የተነሳ የሞታችሁ ነበራችሁ።

11 ሮሜ 8:11

ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ ቢኖር ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በውስጣችሁ በሚኖረው በቅዱስ መንፈሱ አማካይነት ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።

ተዛማጅ ርዕሶች