ስለ ሊቀ ካህናችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ሊቀ ካህናችን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ።
ነገር ግን እርሱ ከኃጢአት በቀር በማንኛውም ነገር እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንምና።
ስለዚህ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትንና የሚረዳንን ጸጋ እንድንቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።
እንደዚህ ያለው ማለትም ኃጢአትና ነቀፋ የሌለበት፣ ንጡሕ፣ ከኃጢአተኞች የተለየ ከሰማያትም በላይ ከፍ ያለ ሊቀ ካህን ሊኖረን ይገባል።
ክርስቶስ በሰው እጆች በተሠራችው ሳይሆን ላቅ ባለችውና ይበልጥ ፍጹምና ቅድስት በመሆነችው፣ ከዚህም ከፍጥረታዊው ዓለም ባልሆነችው ድንኳን በኩል ለመጡት መልካም ነገሮች ሊቀ ካህናት ሆኖ መጥቷል። ክርስቶስ እጅግ ቅድስት ወደሆነችው ስፍራ አንድ ጊዜ ለሰዎች ሁሉ የገባውና የዘላለም ቤዛችንን ያስገኘልን በፍየሎችና በጥጃዎች ደም ሳይሆን በራሱ ደም ነው።
ስለሆነም የእግዚአብሔር በሆነ ነገር ሁሉ መሓሪና ታማኝ ሊቀ ካህን ለመሆንና ለሰዎችም ሁሉ የኃጢአት ይቅርታን ለማስግገኘት በሁሉም ረገድ ወንድሞችን መምሰሉ አስፈላጊ ሆነ።
ክርስቶስ ራሱም ቢሆን ሊቀ ካህናት የመሆንን መብት በገዛ ራሱ አልወሰደም። ይልቁንም እግዚአብሔር ለእርሱ፣ ይህም በሌላ ቦታ፣ እግዚአብሔር፣እንደመልከጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ" ይላል።
ስለዚይ ስለ እነርሱ ሊማልድ ምን ጊዜም በሕይወት ስለሚኖር በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሙሉ በሙሉ ሊያድናቸው ይችላል።
እንግዲህ ልንናገር የፈለግነው ጉዳይ ዋና ነጥቡ ይሄ ነው፦ በሰማያት በልዑል እግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ ሊቀ ካህን አለን።
በእግዚአብሔር ቤት ታላቅ ካህን ስላለን፣
ስለዚህ የሰማያዊ ጥሪ ተከፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች የእምነታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን አስቡ።
በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት ለዘላለም ሊቀ ካህናት በመሆን ኢየሱስ ወደዚህ ስፍራ ለእኛ ቀዳሚ በመሆን ገብቷል።
ኢየሱስ ግን ለዘላለም ስለሚኖር የእርሱ ክህነት የማይለወጥ ነው።