ስለ መልካሙ እረኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ መልካሙ እረኛ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ለበጎቹ ሲል ነፍሱን ይሰጣል።
ያህዌ እረኛዬ ነው፤ ምንም አላጣም፡፡
መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆኑትን ዐውቃቸዋለው፤ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል።
በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔ ዐውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል። የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለው፤ ፈጽሞም አይጠፉም፤ ነጥቆ ከእጄ የሚያወጣቸው ማንም የለም።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። እነሆ፥ እኔ ራሴ በጎቼን እሻለሁ አሰማራቸውማለሁ። እረኛ በተበተኑት በጎች መካከል ባለ ጊዜ መንጋውን እንደሚፈልግ፥ እንዲሁ በጎቼን እፈልጋለሁ በደመናና በጨለማ ቀን ከተበተኑት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ።
በለመለመ መስክ ያሳድረኛል ፀጥ ባለ ውሃ ዘንድ ይመራኛል፡፡ ነፍሴን ይመልሳታል፤ ያድሳታል፡፡ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ ይመራኛል፡፡
አብ እንደሚያውቀኝ፤ እኔም አብን ዐውቀዋለው፤ ነፍሴንም ስለ በጎች እሰጣለሁ።
በሩ እኔ ነኝ። ማንም በእኔ በኩል ቢገባ፣ ይድናል፤ ይገባል፣ ይወጣልም፤ መሰማሪያም ያገኛል።
መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፣ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፣ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።
ቀድሞ ሁላችሁም እንደ ጠፉ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር፤ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።
"ከእናንተ መካከል መቶ በጎች ያሉት ከዚያም ከእነርሱ አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ የጠፋበትን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልግ የማይሄድ ማንነው? ባገኘውም ጊዜ ከመደሰቱ የተነሣ በጫንቃው ይሸከመዋል።
የራሱን ሁሉ ካወጣቸው በኋላ፣ ፊት ፊታቸው ይሄዳል፤ በጎቹም ድምፁን ስለሚያውቁ ይከተሉታል።