ስለ መካከለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ መካከለኛው የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 1 ጢሞቴዎስ 2:5

አንድ እግዚአብሔር አለና፣ እንዲሁም በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል፣ ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ አንድ መካከለኛ አለ፤

02 ዕብራዊያን 9:15

ከዚህም የተነሳ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት በእግዚአብሔር የተጠሩት ስለ ዘላለም ርስት የተሰጣቸውን የስፋ ቃል ይቀበሉ አንድ በመጀመሪያው ኪዳን ሥር ከነበረባቸው የኃጢአት ቅጣት ነፃ እንዲወጡ የሞት ቅጣት ተፈጽሞ ስለነበረ ነው።

03 ዕብራዊያን 12:24

የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደሆነው ኢየሱስና ከአቤል ደም የተሻለውን ወደሚናገር ወደተረጨው ደም ደርሳችኋል።

04 1ኛ ዬሐንስ 2:1

የተወደዳችሁ ልጆቼ ፣ሃጢያት እንዳታደርጉ ይህን እፅፍላችኋላሁ። ግን ማንም ሃጢያት ቢያደርግ ፣ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን ፤እርሱም ፃድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡

05 ገላቲያ 3:20

መካከለኛ ሲል ከአንድ ሰው በላይ እንደሆነ ያመለክታል፥ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።

06 ዕብራዊያን 8:6

ነገር ግን በተሻለ ተስፋ ላይ የተመሠረተ የተሻለ ኪዳን መካከለኛው በመሆኑ ክርስቶስ አሁን የላቀ አገልግሎት ተቀብሏል።

ተዛማጅ ርዕሶች