ስለ ታላቁ እረኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ታላቁ እረኛ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ዕብራዊያን 13:20
እንግዲህ በዘላለም ኪዳን ደም የበጎች ታላቅ እረኛ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስን፣ ከሙታን ያስነሣው የሰላም አምላክ እግዚአብሔር፣በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በእኛ ውስጥ የሚሠራውን፣ በእርሱ ፊት ደስ የሚያሰኘውን ፈቃዱን እንድታደርጉ በማናቸውም መልካም ነገር ያስታጥቃችሁ። ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ክብር ይሁን። አሜን።
02 1ኛ ጴጥሮስ 5:4
የእረኞች ዐለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ።
03 1ኛ ጴጥሮስ 2:25
ቀድሞ ሁላችሁም እንደ ጠፉ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር፤ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።
04 ዮሐንስ 10:11
መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ለበጎቹ ሲል ነፍሱን ይሰጣል።
ያህዌ እረኛዬ ነው፤ ምንም አላጣም፡፡
06 ዮሐንስ 10:14
መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆኑትን ዐውቃቸዋለው፤ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል።
07 ኢሳይያስ 40:11
መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፣ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፣ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።
08 ሕዝቅኤል 34:23
በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ እርሱም ያሰማራቸዋል፥ እርሱም ባሪያዬ ዳዊት ነው! ያሰማራቸዋል እረኛም ይሆናቸዋል።