ስለ የነገሥታት ንጉሥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የነገሥታት ንጉሥ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ልብሱና ጭኑ ላይ፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ የሚል ስም ተጽፎበት ነበር።
እርሱም መገለጡን የተባረከውና፣ ብቻውን ኃያል የሆነው፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ በወሰነው በትክክለኛው ጊዜ ያሳያል፡፡
በጉን ይዋጋሉ። ይሁን እንጂ፣ በጉ የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ በመሆኑ እርሱ ያሸንፋቸዋል የተጠሩት፣ የተመረጡትና ታማኝ የሆኑት ከእርሱ ጋር ድል ይነሣሉ።”
እናንተ ደጆች ራሳችሁን ቀና አድርጉ እናንተ የዘላለም በሮች የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ! ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? ብርቱና ኃያል የሆነው ያህዌ፣ በጦርነት አሸናፊ የሆነው ያህዌ ነው፡፡
ሥልጣን፣ ክብርና ታላቅ ኃይል ተሰጠው፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች፤ መንግሥታትና ሕዝቦች ሰገዱለት፤ ግዛቱም ለዘላለም የማያልፍ ነው፤ መንግሥቱም ፈጽሞ የማይጠፋ ነው።
ሰባተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤በሰማይም«የዓለም መንግሥት የጌታ አምላካችንና የእርሱ ክርስቶስ ሆናለች፤ እርሱም ለዘላለም ይነግሣል» የሚል ታላቅ ድምጽ ሰማሁ።
እግዚአብሔር የምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና ስለዚህ በማስተዋል ዘምሩለት፡፡ እግዚአብሔር በሕዝቦች ሁሉ ነግሦአል እግዚአብሔር በተቀደሰ ዙፋኑ ላይ ተቀምጧል፡፡
ስለዚህ ለዘላለም ንጉሥ ፣ ለማይሞተው እና ለማይታየው፣ ብቻውን አምላክ ለሆነው፣ ክብርና ግርማ ለዘላለም ይሁን፡፡ አሜን፡፡
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፣ እጅግ ደስ ይበልሽ! አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፣ በደስታ ጩኺ! እነሆ ንጉሥሽ በጽድቅ ወደ አንቺ መጥቶ ያድንሻል። እርሱ ትሑት ነው፤ በእህያ ላይ ይቀመጣል፤ በአህያ ግልገል በውርንጫዋ ላይ ይቀመጣል።
«እኔ ራሴ በጽዮን፣ በተቀደሰውም ተራራዬ ንጉሤን ሾምሁ፡፡»
ሕፃን ተወልዶልናልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፣ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።