ስለ ጠበቃችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ጠበቃችን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
የተወደዳችሁ ልጆቼ ፣ሃጢያት እንዳታደርጉ ይህን እፅፍላችኋላሁ። ግን ማንም ሃጢያት ቢያደርግ ፣ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን ፤እርሱም ፃድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡
የሚኮንንስ ማነው? ስለ እኛ የሞተው፥ ይልቁንም ደግሞ ከሞት የተነሣው ክርስቶስ ነው። እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር በክብር ሥፍራ ይገዛል፥ስለ እኛም እየማለደልን ያለው እርሱ ነው።
ስለዚይ ስለ እነርሱ ሊማልድ ምን ጊዜም በሕይወት ስለሚኖር በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሙሉ በሙሉ ሊያድናቸው ይችላል።
አንድ እግዚአብሔር አለና፣ እንዲሁም በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል፣ ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ አንድ መካከለኛ አለ፤
ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፣ ከብዙ ኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፣ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፣ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
ክርስቶስ በእጅ ወደተሠራው የእውነተኛውም ግልባጭ ብቻ ወደነበረው ቅድስተ ቅዱሳን አልገባምና። ይልቁንም እርሱ የገባው እግዚአብሔር ባለበት ስለ እኛ አሁን እግዚአብሔር ፊት ወደሚቀርብበት ሰማይ በቀጥታ ገብቷል።
እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ። ነገር ግን እርሱ ከኃጢአት በቀር በማንኛውም ነገር እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንምና። ስለዚህ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትንና የሚረዳንን ጸጋ እንድንቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።
እነርሱ የአንተ ናቸውና አንተ ለሰጠኸኝ ለእነርሱ እንጂ ለዓለም አልጸልይም፡፡
ኢየሱስ ግን ለዘላለም ስለሚኖር የእርሱ ክህነት የማይለወጥ ነው። ስለዚይ ስለ እነርሱ ሊማልድ ምን ጊዜም በሕይወት ስለሚኖር በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሙሉ በሙሉ ሊያድናቸው ይችላል።
ከዚያም ሊቀ ካሁኑ ኢያሱ በያህዌ መልአክ ፊት ቆሞ ያህዌ አሳየኝ፤ እርሱን በኃጢአት ልመክሰሰ ሰይጣን በቀኙ በኩል ቆሞ ነበር። የያህዌ መልአክ ሰይጣንን፣ “አንተ ሰይጣን ያህዌ ይገሥጽህ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠ ያህዌ ይገሥጽህ! ይህ ሰው ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይድለምን?” አለው።
እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይኮንናቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው። የሚኮንንስ ማነው? ስለ እኛ የሞተው፥ ይልቁንም ደግሞ ከሞት የተነሣው ክርስቶስ ነው። እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር በክብር ሥፍራ ይገዛል፥ስለ እኛም እየማለደልን ያለው እርሱ ነው።
እርሱ የእኛ ብቻ ሳይሆን፣ የዓለሙም ሁሉ ሃጢዓት ማስተስረያ ነው፣፡፡
የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደሆነው ኢየሱስና ከአቤል ደም የተሻለውን ወደሚናገር ወደተረጨው ደም ደርሳችኋል።
አሁንም ቢሆን፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፥ ለእኔም የሚሟገትልኝ በአርያም ነው።