ስለ ጭቆና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ጭቆና የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
መልካም ማድረግን ተማሩ፣ ፍርድን ፈልጉ፣ የተጨቆነውን እርዱ፣ አባት ለሌለው ፍረዱለት፣ ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ።"
ያህዌ ለተጨቆኑት ዐምባ ነው፡፡ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል፡፡
ያህዌ ለተጨቆኑ ሁሉ፣ ቅን ፍርድንና ፍትሕን ይሰጣል፡፡
እንደገና ከፀሐይ በታች ስለሚደረገው ግፍ ሁሉ አሰብሁ። የሚጨቆኑትን ሰዎች ዕንባ ተመልከቱ። የሚያጽናናቸውም የለም። በጨቋኞቻቸው እጅ ኃይል አለ፥ ነገር ግን የተጨቆኑት ሰዎች አጽናኝ የላቸውም።
መበለቶችንና ድኻ አደጎችን፣ መጻተኞችንና ድኻውን አታስጨንቋቸው፤ በልባችሁም አንዳችሁ በሌላው ክፉ አታስቡ!
ድሃ በመሆኑ ምክንያት ድሃ ሰው አትዝረፍ፣ ችግረኛውንም በበር ላይ አትግፋው፣ እግዚአብሔር ለእነርሱ ይፈርድላቸዋልና፣ የዘረፏቸውንም ሰዎች ሕይወት እርሱ ይነጥቃል፡፡
«ስለ ድኾች መከራ፣ ስለ ችግረኞች ጩኸት ያህዌ አሁን እነሣለሁ፤ የናፈቁትንም ሰላም እሰጣቸዋለሁ» ይላል፡፡
ለተቸገረው ሕዝብ ይሟገታል የችግረኞችን ልጆች ያድናል ጨቋኙንም ያደቀዋል፡፡
መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፣ ድሀ አደጎችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፣ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፣ የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፣ ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!
ድሀን የሚያስጨንቅ ሰው ፈጣሪውን ይሰድባል፣ ለድሀ ቸርነትን የሚያሳይ ግን ፈጣሪውን ያከብራል፡፡
ለተጨቆኑት የሚፈርድ፣ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፡፡ ያህዌ እስረኞችን ነጻ ያወጣል፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፣ የተዘረፈውንም ከጨቋኙ እጅ አድኑ። በምድራችሁ ያለውን እንግዳ፣ ወይም የትኛውንም ወላጅ አልባ ወይም መበለቲቱን አትበድሉ። አታምፁባቸው፣ ወይም በዚህ ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።
ድኻውን ረግጣችኋልና፥ የስንዴውን ም ድርሻ ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ብትሠሩም አትኖሩባቸውም። ያማሩ የወይን ተክል ቦታዎች አሉአችሁ፥ የወይን ጠጃቸውን ግን አትጠጡም።