ስለ ፍትሕ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ፍትሕ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

ሰው ሆይ፣ መልካሙን፣ ያህዌ ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል ፍትሕ አድርግ፤ ደግነትን ውደድ፤ ከአምላክህ ጋር በትሕትና ተመላለስ፡፡

02 ኢሳይያስ 1:17

መልካም ማድረግን ተማሩ፣ ፍርድን ፈልጉ፣ የተጨቆነውን እርዱ፣ አባት ለሌለው ፍረዱለት፣ ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ።"

03 አሞጽ 5:24

በዚያ ፈንታ ፍትሕ እንደ ውኃ፥ ጽድቅም ሳያቋርጥ እንደሚመነጭ ምንጭ ይፍሰስ።

04 ምሳሌ 21:3

ከመስዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አለው፡፡

በሕይወት እንድትኖሩና እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣችሁን ምድር እንድትወርሱ ቅን ፍርድን ብቻ ተከተሉ።

06 ዘካርያስ 7:9

“የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ‘በእውነተኛ ፍትሕና የኪዳን ታማኝነት፣ በምሕረትም ፍረዱ። እያንዳንዱ ሰው ለወንድሙ እንዲህ ያድረግ።

እርሱ ጽድቅንና ፍትሕን ይወዳል ምድር በያህዌ ኪዳን ታማኝት ተሞልታለች፡፡

08 ኢሳይያስ 30:18

ይሁን እንጂ እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፣ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብሩካን ናቸው።

09 ምሳሌ 31:9

ትክክል ስለሆነው ነገር ጮህ ብለህ ተናገር፣ ፍርድም ስጥ፣ ስለ ድሆችና ስለ ተቸገሩም ሰዎች ጉዳይ መልስ ስጥ፡፡

10 ኤርሚያስ 22:3

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፣ የተዘረፈውንም ከጨቋኙ እጅ አድኑ። በምድራችሁ ያለውን እንግዳ፣ ወይም የትኛውንም ወላጅ አልባ ወይም መበለቲቱን አትበድሉ። አታምፁባቸው፣ ወይም በዚህ ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።

ዘወትር መልካሙንና ትክክል የሆነውን የሚያደርጉ የተባረኩ ናቸው፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች