ስለ መበለቲቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ መበለቲቱ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
በተቀደሰ ማደሪያው ያለው አምላክ አባት ለሌላቸው አባት ነው፡፡ ለመበለቶችም ዳኛ ነው፡፡
በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት ንጹሕና ርኵሰት የሌለበት ሃይማኖት ይህ ነው፤ አባት የሌላቸውንና መበለቶችን በችግራቸው መርዳት፤ በዓለም ካለ ርኵሰት ራስን መጠበቅ።
እግዚአብሔር ለድሃ አደጉና ባል ለሞተባት ይፈርዳል፥ ምግብና ልብስም የሚሰጥ ነው።
መልካም ማድረግን ተማሩ፣ ፍርድን ፈልጉ፣ የተጨቆነውን እርዱ፣ አባት ለሌለው ፍረዱለት፣ ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ።"
ማንኛዋንም መበለት ወይም አባትና እናት የሌለውን ልጁ ማስጨነቅ የለባችሁም።
ያህዌ መጻተኞን በምድር ይጠብቃል ደኸ አደጐችንና መበለቶችን ይደግፋል፡፡ የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል፡፡
የእርሻችሁን ሰብል በምታጭዱበት ጊዜ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፥ ያን ለመውሰድ ተመልሳችሁ አትሂዱ፤እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ ሥራ ሁሉ እንዲባርካችሁ ነዶውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ተዉ።
በትክክል መበለት የሆኑትን አክብር፤
ድሀ አደጎችህን ተዋቸው። እኔም ለሕይወታቸው እንክብካቤ አደርጋለሁ፤ መበለቶችህም በእኔ ሊታመኑ ይችላሉ።"
መበለቶችንና ድኻ አደጎችን፣ መጻተኞችንና ድኻውን አታስጨንቋቸው፤ በልባችሁም አንዳችሁ በሌላው ክፉ አታስቡ!
እግዚአብሔር የትዕቢተኛውን ውርስ ያፈራርሳል፣ የመበለቲቱን ንብረት ግን ይጠብቃል፡፡
ጌታም ተመልክቷት እጅግ ዐዘነላትና፣ “አታልቅሺ” አላት።
በአገራችሁም ደጅ ያለ መጻተኛ፥ ድሀ አደግ፥ ባል የሞተባት መጥተው ይበላሉ፤ ይጠግባሉም። ይኸውም እግዚአብሔር አምላካችሁ በምታደርጉት በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ይባርካችሁ ዘንድ ነው።
ከዚያም አንዲት ድኻ መበለት መጥታ ሁለት ናስ ጨመረች፤ይህም የብር ሩብ ነው፡፡ እርሱም ደቀመዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ይህች መበለት በመባ መቀበያው ውስጥ ገንዘባቸውን ከጨመሩት ሁሉ አብልጣ ሰጠች፡፡