ስለ ወላጅ አልባ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ወላጅ አልባ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት ንጹሕና ርኵሰት የሌለበት ሃይማኖት ይህ ነው፤ አባት የሌላቸውንና መበለቶችን በችግራቸው መርዳት፤ በዓለም ካለ ርኵሰት ራስን መጠበቅ።
በተቀደሰ ማደሪያው ያለው አምላክ አባት ለሌላቸው አባት ነው፡፡ ለመበለቶችም ዳኛ ነው፡፡
እግዚአብሔር ለድሃ አደጉና ባል ለሞተባት ይፈርዳል፥ ምግብና ልብስም የሚሰጥ ነው።
አሦር አያድነንም፤ ለጦርነትም ፈረሶችን አንጋልብም። ወይም ከእንግዲህ የእጆቻችንን ሥራዎች 'እናንተ አምላኮቻችን ናችሁ' አንላቸውም፤ አባት አልባው እንኳ በአንተ ዘንድ ርኅራኄን ያገኛልና።
አንተ ግን መከራንና ሐዘንን ታያለህ ምስኪኑም ራሱን በአንተ ላይ ይጥላል፤ ለድኻ አደጉም አንተ ረዳቱ ነህ፡፡
ያህዌ መጻተኞን በምድር ይጠብቃል ደኸ አደጐችንና መበለቶችን ይደግፋል፡፡ የክፉዎችን መንገድ ግን ያጠፋል፡፡
ማንኛዋንም መበለት ወይም አባትና እናት የሌለውን ልጁ ማስጨነቅ የለባችሁም።
ድሀ አደጎችህን ተዋቸው። እኔም ለሕይወታቸው እንክብካቤ አደርጋለሁ፤ መበለቶችህም በእኔ ሊታመኑ ይችላሉ።"
መልካም ማድረግን ተማሩ፣ ፍርድን ፈልጉ፣ የተጨቆነውን እርዱ፣ አባት ለሌለው ፍረዱለት፣ ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ።"
መጻተኛው ወይም አባት ለሌለው ልጅ ፍትሕ አትንፈጉት፤ ባል የሞትባትንም መደረቢያ መያዣ አታድርጉ።
አባትና እናቴ ቢተውኝ እንኳ ያህዌ ይቀበለኛል፡፡
መበለቶችንና ድኻ አደጎችን፣ መጻተኞችንና ድኻውን አታስጨንቋቸው፤ በልባችሁም አንዳችሁ በሌላው ክፉ አታስቡ!