ስለ አፍህን ጠብቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ አፍህን ጠብቅ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ሰው ራሱን ከመከራ ይጠብቃል፡፡
ያህዌ ሆይ፣ ለአፌ ጠባቂ አኑር የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ
አፉን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፣ ከንፈሮቹን ያለ ልክ የሚከፍት ግን ይጠፋል፡፡
አንድ ሰው ሃይማኖተኛ ነኝ እያለ፣ አንደበቱን ግን ባይቆጣጠር፣ ልቡን ያስታል፤ ሃይማኖቱም ከንቱ ነው።
እኔ፣ «በአንደበቴ እንዳልበድል ለምናገረው እጠነቀቃለሁ፣ በክፉዎችም ፊት እስካለሁ ድረስ፣ በአፌ ልጓም አደርጋለሁ» አልሁ፡፡
በብዙ ቃላቶች ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፣ ለሚናገረው ነገር ጥንቃቄ የሚደርግ ሰው ግን ጥበበኛ ነው፡፡
ሞኝ እንኳ ዝም ሲል ጥበበኛ እንደሆነ ይታሰባል፤ አፉንም ዘግቶ ዝም ሲል፣ እንደ ምሁር ይቆጠራል፡፡
ለመናገር እጅግ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔር ፊት የትኛውንም ጉዳይ ለማቅረብ ልብህ እጅግ አይፍጠን። እግዚአብሔር በሰማይ ነው፥ አንተ ግን በምድር፤ ስለዚህ ቃልህ ጥቂት ይሁን።
ለእናንተም እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ሰዎች ስለ ተናገሯቸው ከንቱ ንግግሮች መልስ ይሰጣሉ፡፡
የለፍላፊ ሰው ቃሎች እንደሚዋጋ ሰይፍ ነው፣ የጥበበኛ አንደበት ግን ፈውስን ያመጣል፡፡
ጠማማ ንግግርን ከአንተ አስወግድ፣ ብልሹ ወሬ ከአንተ አርቅ፡፡
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን ዕወቁ። ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገዬ፣ ለመቆጣትም የዘገዬ ይሁን!
ሞትና ሕይወት በምላስ ላይ ናቸው፣ የሚወዱትም ፍሬዋን ይበላሉ፡፡
አንደበትህ ሰውነትህን ለኃጢአት እንዲያነሣሣው አትፍቀድለት። ለካህኑ መልዕክተኛ፥ "ያ ስዕለት ስሕተት ነበረ" አትበል። በሐሰት በመሳል እግዚአብሔርን ለምን ታስቆጣዋለህ፥ የእጅህንስ ሥራ እንዲያጠፋ እግዚአብሔርን ለምን ታነሣሣዋለህ?
በቃሎቹ የሚቸኩለውን ሰው ተመልክተሃል? ከእርሱ ይልቅ ለሞኝ የበለጠ ተስፋ አለው፡፡