ስለ ወደ እግዚአብሔር መጮህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ወደ እግዚአብሔር መጮህ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

ጻድቃን ወደ ያህዌ ይጮኻሉ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል፡፡

በጨነቀኝ ጊዜ ያህዌን ጠራሁት፤ እንዲረዳኝም ወደ አምላኬ ጮኽሁ፤ ከመቅደሱ ድምፄን ሰማ፤ ጩኸቴም ከፊቱ ደረሰ፤ ወደ ጆሮውም ገባ፡፡

በጨነቀኝ ጊዜ ወደ ያህዌ ተጣራሁ እርሱም መለሰልኝ፡፡

04 ዮናስ 2:2

እንዲህ አለ፤ «ተጨንቄ ሳለሁ ወደ ያህዌ ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ፤ እርሱ እንዲረዳኝ ከጥልቁ መቃብር ጮኽኩ አንተም ጩኸቴን ሰማህ፡፡

ያህዌ ለሚጠሩት ሁሉ በእምነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፡፡

በትዕግሥት ያህዌን ደጅ ጠናሁት እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማኝ፡፡

አንተ ስለምትመልስልኝ በመከራዬ ቀን ወደ አንተ እጣራለሁ፡፡

ድምፄን ከፍ አድርጌ ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ ይሰማኝ ዘንድ ድምፄን ከፍ አድርጌ እግዚአብሔርን እጠራለሁ፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች