ስለ ምልጃ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ምልጃ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 1 ጢሞቴዎስ 2:1
ስለዚህ ከሁሉ በፊት፣ ጸሎት፣ ምልጃና ምሥጋና ስለ ሰዎቸ ሁሉ እንዲደረግ እመክራለሁ፤ እግዚአብሔርን በመፍራትና በማክበር፣
02 ያዕቆብ 5:16
እንዲሁ ጌታ ከበሽታ ሊፈውስና ኃጢአትን ይቅር ሊል ስለሚችል ያደረጋችሁትን ኃጢአት በተመለከተ አንዳችሁ ለሌላችሁ ተናዘዙ፡፡ ጻድቃን ሰዎች ከጸለዩና አንድ ነገር እንዲያደርግላቸው ጌታን አጥብቀው ከጠየቁት፣ እግዚአብሔር ይገለጣል፤ ደግሞም በእርግጠኝነት ያን ነገር ያደርገዋል፡፡
03 ኤፌሶን 6:18
ዓይነት ጸሎትና ልመና ሁልጊዜ በመንፈስ በመጸለይና መልሱን ከእርሱ በመጠበቅ፥ ለቅዱሳንም ልመና በማቅረብ ትጉ።
04 ሮሜ 8:26
እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በድካማችን ውስጥ ያግዘናል። እንዴት መጸለይ እንደሚገባን ስለማናውቅ መንፈስ ቅዱስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይቻል መቃተት ስለ እኛ ይማልድልናል።
05 ቆላስይስ 4:2
በንቃት እግዚአብሔርን እያመሰገናችሁ ሳታቋርጡ ጸልዩ።
ስለዚህ ከሁሉ በፊት፣ ጸሎት፣ ምልጃና ምሥጋና ስለ ሰዎቸ ሁሉ እንዲደረግ እመክራለሁ፤ እግዚአብሔርን በመፍራትና በማክበር፣ በጸጥታ ሕይወት ሰላማዊ ኑሮ እንድንኖር፣ ለነገሥታትና በሥልጣን ላይ ላሉ ሁሉ ጸልዩ፡፡
07 ኢዮብ 42:10
ኢዮብ ስለ ጓደኞቹ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔር እንደገና አበለጸገው። ቀድሞ ከነበረው በላይ እግዚአብሔር ዕጥፍ አድርጎ ሰጠው።