ስለ በጸሎት ድፍረት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ በጸሎት ድፍረት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዕብራዊያን 4:16

ስለዚህ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትንና የሚረዳንን ጸጋ እንድንቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።

02 ኤፌሶን 3:12

በክርስቶስ በማመናችን በእርሱ ሆነን በድፍረትና በልበ ሙሉነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለንና።

03 1ኛ ዬሐንስ 5:14-15

በእርሱ ፊት ያለን ድፍረት ይህ ነው፣እንደ ፈቃዱ ማንኛውንም ነገር ብንጠይቀው፣ይሰማናል። የምንጠይቀውን ሁሉ እንደሚሰማን ካወቅን፣ከርሱ የጠየቅነውን ሁሉ እንደተቀበልን እናውቃለን።

04 ዕብራዊያን 10:19

ስለዚህ ወንድሞች፣ በኢየሱስ ደም አማካኝነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የመግባት ድፍረት አለን።

05 ያዕቆብ 1:5-6

ከእናንተ አንዱ ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ከፈለገ፣ በሚጠይቀው ላይ ሳይቈጣ በልግሥና የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይጠይቅ፡፡ እግዚአብሔርን ስትለምኑ፣ የምትጠይቁትን እንደሚሰጣችሁ እመኑ፤ መልስ እንደሚሰጣችሁና ሁልጊዜም እንደሚረዳችሁ አትጠራጠሩ፤ የሚጠራጠሩ ሰዎች እግዚአብሔርን ሊከተሉት አይችሉም፤ መጠራጠር ልክ ተመልሶ እንደሚመጣ፣ ደግሞም በዚያው አቅጣጫ መጓዝን እንደማይቀጥል የባሕር ማዕበል ያለ ነገር ነው፡፡

06 ዕብራዊያን 10:22

ልባችን በመረጨት ከክፉ ኅሊና ሁሉ ነጽቶ፣ ሥጋችንም በንጹሕ ውኃ ታጥቦ ባገኘነው የእምነት ሙሉ ዋስትና በእውነተኛ ልብ እንቅረብ።

07 1ኛ ዬሐንስ 3:21-22

ወዳጆች ሆይ! ልባችን የማይፈርድብን ከሆነ፣በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት አለን። ትዕዛዙን የምንጠብቅና፣በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆነ፣ የምንለምነውንና ሁሉ እንቀበላለን፡፡

08 ማርቆስ 11:24

ስለዚህ እላችኋለሁ፤የጸለያችሁትንና የለመናችሁትን ነገር ሁሉ እንደምትቀበሉ ብታምኑ ይሆንላችሁማል፡፡

09 የማቴዎስ 7:7-8

ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፥ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል። የሚለምን ሰው ሁሉ ይቀበላልና፣ የሚፈልግ ሰውም ያገኛል፥ ለሚያንኳኳም ሰው ይከፈትለታል።

10 ዮሐንስ 14:13-14

አብ በልጁ ይከብር ዘንድ ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ። ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ፣ እኔ አደርገዋለሁ።

11 ኤፌሶን 2:18

በኢየሱስ አማካይነት እኛ ሁለታችንም በአንድ መንፈስ ወደ አብ መቅረብ እንችላለንና።

ተዛማጅ ርዕሶች