ስለ ሙሾ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ሙሾ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ያህዌ ሆይ፣ እስከ መቼ ድረስ ለዘላለሙ ትረሳኛለህ? ፊትህን ከእኔ የምትሰውረውስ እስከመቼ ድረስ ነው?
ነፍሴ ሆይ፣ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? የመድኃኒቴን አምላክ ዳግመኛ እንዳመሰግነው እግዚአብሔርን ተስፋሽ አድርጊ፡፡
ሰዎች ሆይ፣ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ በፊቱም ልባችሁን አፍስሱ እግዚአብሔር ለእኛ መጠጊያችን ነውና፡፡ ሴላ
ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት የተነሳ ነው፥ የምሕረቱ ሥራዎች አያልቁምና። የምሕረቱ ሥራዎች ማለዳ ማለዳ አዲስ ናችው፤ ታማኝነትህ ምንኛ ታላቅ ነው!
ቁጣው ለአጭር ጊዜ ነው ሞገሱ ግን ለዕድሜ ልክ ነው፡፡ ሌሊት ሲለቀስ አድሮ ማለዳ ደስታ ይሆናል፡፡