ስለ ጸሎት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ጸሎት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፤ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አስታውቁ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ። ጌታ ቅርብ ነውና።
አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ጓዳህ ገብተህ በር ዝጋና በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል፡፡
ባለማቋረጥ ጸልዩ፣
እንዲሁ ጌታ ከበሽታ ሊፈውስና ኃጢአትን ይቅር ሊል ስለሚችል ያደረጋችሁትን ኃጢአት በተመለከተ አንዳችሁ ለሌላችሁ ተናዘዙ፡፡ ጻድቃን ሰዎች ከጸለዩና አንድ ነገር እንዲያደርግላቸው ጌታን አጥብቀው ከጠየቁት፣ እግዚአብሔር ይገለጣል፤ ደግሞም በእርግጠኝነት ያን ነገር ያደርገዋል፡፡
ስለዚህ እላችኋለሁ፤የጸለያችሁትንና የለመናችሁትን ነገር ሁሉ እንደምትቀበሉ ብታምኑ ይሆንላችሁማል፡፡
ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፥ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።
'ወደ እኔ ጩኽ፣ እኔም እመልስልሃለሁ። አንተም የማታስተውለውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ።'
ያህዌ ለሚጠሩት ሁሉ በእምነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፡፡
ከዚያም ኢየሱስ ሳይታክቱ ዘወትር መጸለይ እንደሚገባቸው እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፤
በንቃት እግዚአብሔርን እያመሰገናችሁ ሳታቋርጡ ጸልዩ።
እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፣ ለምኑ፣ ደስታችሁም ሙሉ ይሆን ዘንድ ትቀበላላችሁ፡፡
በማታ፣ በጧትና በቀትር አቃሥታለሁ እቃትታለሁም እርሱም ድምፄን ይሰማል፡፡
አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ።”
በእርሱ ፊት ያለን ድፍረት ይህ ነው፣እንደ ፈቃዱ ማንኛውንም ነገር ብንጠይቀው፣ይሰማናል።