ስለ በእግዚአብሔር መታመን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ በእግዚአብሔር መታመን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ምሳሌ 3:5-6

በሙሉ ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል ላይ አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፣ እርሱም መንገድህን ቀና ያደርገዋል፡፡

መንገድህን ለያህዌ አደራ ስጥ በእርሱ ታመን እርሱም ያከናውንልሃል፡፡

03 ኢሳይያስ 26:3

በአንተ ታምናለችና በአንተ ለምትጸና አእምሮ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።

ስምህን የሚያውቁ በአንተ ይታመናሉ አንተ ያህዌ፣ የሚፈልጉህን አትተዋቸውም፡፡

05 ትንቢተ ናሆም 1:7

ያህዌ መልካም ነው፤ በመከራ ጊዜም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑበት ታማኝ ነው፡፡

እኔ ግን ፍርሃት ሲይዘኝ እምነቴን አንተ ላይ አደርጋለሁ

07 ኤርሚያስ 17:7-8

ነገር ግን በእግዚአብሔር የታመነ፣ የልበ-ሙሉነቱ ምክንያት እግዚአብሔር ነውና ቡሩክ ነው። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፣ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ተክል ይሆናልና። ሙቀት ሲመጣ አያይም፣ ቅጠሉ ይለመልማልና። ከዚያም፣ በድርቅ ዓመት ላይ አይሠጋም፣ ማፍራቱንም አያቋርጥም።

አንዳንዶች በሰረገላ ሌሎች በፈረስ ይታመናሉ እኛ ግን የያህዌን ስም እንጠራለን፡፡

በሰው ከመታመን ይልቅ ያህዌን መከታ ማድረግ ይሻላል፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች