ስለ እምነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ እምነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ዕብራዊያን 11:1
እንግዲህ እምነት ሰው በተስፋ ለሚጠበቀው ነገር ማረጋገጫ ያልታየውም ነገርም አስረጅ ነው።
02 ሮሜ 10:17
ስለዚህ እምነት የሚመጣው ከመስማት ሲሆን መሰማት ያለበትም የክርስቶስ ቃል ነው።
03 ኤፌሶን 2:8
የዳናችሁት በእምነት አማካይነት በጸጋ ነውና ፤ ይህ ከእግዚአብሔር ያገኛችሁት ስጦታ እንጂ ከእናንተ የሆነ ነገር አይደለም።
04 2ኛ ቆሮንቶስ 5:7
ምክንያቱም በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና።
05 ዕብራዊያን 11:6
ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም፣ ወደ እግዚአብሔር የሚመጣ፣ እግዚአብሔር እንዳለና እርሱን ለሚሹትም ዋጋን እንደሚሰጥ ማመን ስለሚገባው ነው።
06 ማርቆስ 11:22
ኢየሱስም እንዲህ አለው፡፡ በእግዚአብሔር እመን፤
07 ገላቲያ 2:20
ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።
08 1ኛ ዬሐንስ 5:4
ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። ዓለምን የሚያሽንፈው እምነታችን ነው።
09 ዕብራዊያን 11:3
ፍጥርተ-ዓለሙ በእግዚአብሔር ትእዛዝ መፈጠሩን፣ የሚታየውም ከሚታዩት ነገሮች የተፈጠረ አለመሆኑን በእምነት እንረዳለን።