ስለ በእምነት መመላለስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ በእምነት መመላለስ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 2ኛ ቆሮንቶስ 5:7
ምክንያቱም በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና።
02 ዕብራዊያን 11:6
ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም፣ ወደ እግዚአብሔር የሚመጣ፣ እግዚአብሔር እንዳለና እርሱን ለሚሹትም ዋጋን እንደሚሰጥ ማመን ስለሚገባው ነው።
03 ሮሜ 1:17
"ጻድቅ በእምነት ይኖራል" ተብሎ እንደተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ በወንጌል ከእምነት ወደ እምነት ተገልጧልና።
04 ገላቲያ 2:20
ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።
05 ቆላስይስ 2:6
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ።
06 ዕብራዊያን 11:8
አብርሃም በተጠራ ጊዜ ርስትን ወደሚቀበልበት ቦታ ታዞ የሄደው በእምነት ነበር። የወጣው ወዴት እንደሚሄድ ሳያውቅ ነበር።
07 ዕንባቆም 2:4
ተመልከት! ጠማማ ሐሳብ ያለው ሰው ታብዮአል፡፡ ጻድቁ ግን በእምነቱ ይኖራል፡፡
08 ሮሜ 4:20-21
ነገር ግን አብርሃም ከእግዚአብሔር ተስፋ የተነሣ በእምነት ዕጦት አላመነታም። ከዚህ ይልቅ በእምነት በረታ፥ ለእግዚአብሔርም ምስጋናን ሰጠ። እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ሊፈጽመው ደግሞ እንደሚችል በጥብቅ ተረዳ።