ስለ በእግዚአብሔር መተማመን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ በእግዚአብሔር መተማመን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ፊልጵስዩስ 1:6

ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ውስጥ የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመለስ ቀን ድረስ እንደሚፈጽም እርግጠኛ ነኝ።

02 ዕብራዊያን 13:6

ስለዚህ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም። ሰውስ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” ብለን በድፍረት እንናገራለን።

ያህዌ ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው? ያህዌ የሕይወቴ መታመኛዋ ነው የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?

04 1ኛ ዬሐንስ 5:14

በእርሱ ፊት ያለን ድፍረት ይህ ነው፣እንደ ፈቃዱ ማንኛውንም ነገር ብንጠይቀው፣ይሰማናል።

05 ዕብራዊያን 4:16

ስለዚህ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትንና የሚረዳንን ጸጋ እንድንቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።

06 ምሳሌ 3:26

እግዚአብሔር በአጠገብህ ይሆናልና፣ እግርህም በወጥመድ እንዳያያዝ ይጠብቅሃልና፡፡

ያህዌ ከእኔ ጋር ነው፤ አልፈራም ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?

08 ፊልጵስዩስ 4:13

ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።

09 2 ጢሞቴዎስ 1:12

ስለዚህ ምክንያት እኔ መከራ እቀበላለሁ፣ ነገር ግን አላፍርበትም፣ ያመንኩትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትን አደራ እስከዚያች ቀን ድረስ እንደሚጠብቅ ተረድቼአለሁ፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች