ስለ ቤዛነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ቤዛነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኤፌሶን 1:7

እንደ ጸጋው ባለጠግነት መጠን በሚወደው ልጁ ደም ቤዛነትን ይኸውም የሐጢአት ይቅርታን አገኘን።

02 ቆላስይስ 1:13-14

ከጨለማ ኅይል አዳነን፤ ወደ ተወደደውም ወደ ልጁ መንግሥት አሸጋገረን። በልጁም የኅጢአታችንን ይቅርታ፣ ድነትን አገኘን።

03 ቲቶ 2:14

ኢየሱስ ራሱን ለእኛ የሰጠው፣ ከዓመፅ ነፃ ሊያወጣንና ሊያነፃን፣ ገንዘቡና መልካምን ለማድረግ የሚናፍቅ ሕዝብ፣ ለራሱ ሊያደርገን፣ ዋጋ ለመክፈል ነው።

04 1ኛ ጴጥሮስ 1:18-19

ከቀድሞ አባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከማይረባ ሕይወት የተዋጃችሁት በሚጠፋ ነገር ማለትም በብር ወይም በወርቅ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ፤ ይልቁንም የተዋጃችሁት ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ ደም፣ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው።

05 ገላቲያ 3:13

«በእንጨት ላይ የሚሰቀል የተረገመ ነው» ተብሎ በተጻፈው መሰረት እርሱ ስለኛ እርግማን በመሆን ከህግ እርግማን ዋጀን።

06 ሮሜ 3:24

በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በተደረገው ቤዛነት በነጻ በጸጋው ይጸድቃሉ።

07 1ኛ ቆሮንቶስ 6:20

በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም። ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።

08 ዕብራዊያን 9:12

ክርስቶስ እጅግ ቅድስት ወደሆነችው ስፍራ አንድ ጊዜ ለሰዎች ሁሉ የገባውና የዘላለም ቤዛችንን ያስገኘልን በፍየሎችና በጥጃዎች ደም ሳይሆን በራሱ ደም ነው።

09 ሮሜ 8:23

ይህም ብቻ አይደለም፥ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ የመጀመሪያው ፍሬ ያለን እኛ፥የሰውነታችን ቤዛ የሚሆነውን ልጅነታችንን እየተጠባበቅን እኛ ራሳችን እንኳን በውስጣችን እንቃትታለን።

10 ሉቃስ 1:68

“የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፣ የመቤዠት ሥራ በመሥራት ሕዝቡን ረድቶታልና፡፡

እነርሱም እንዲህ የሚል አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤«መጽሓፉን ትወስድ እና ማኅተሞቹን ተፈታ ዘንድ ይገባሃል፤ ታርደሃልና በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ፥ከቋንቋ ሁሉ፥ ከሕዝብና ከአገር ሁሉ ሰዎችን ዋጅተሃል።

ያህዌ መሓሪ ነው፤ ይቅር ለማለትም ፈቃደኛ ነው እስራኤል ሆይ፣ ያህዌን ተስፋ አድርግ፡፡

13 1ኛ ቆሮንቶስ 1:30

በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእግዚአብሔር ሥራ የተነሳ ነው፤ እርሱም ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፤ጽድቃችንና ቅድስናችን ቤዛችንም ሆኖአልና።

ተዛማጅ ርዕሶች