ስለ እርቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ እርቅ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እነዚህ ነገሮች ሁሉ የሆኑት እኛን በክርስቶስ ከራሱ ጋር ባስታረቀንና የዕርቅ አገልግሎት በሰጠን በእግዚአብሔር ነው።
ጠላቶች እያለን በልጁ ሞት ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቅን ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን።
እግዚአብሔርም በደላቸውን ሳይቆጥርባቸው ዓለሙን በክርስቶስ ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበር። እኛንም ለዚህ የዕርቅ መልዕክት ታማኝ አድርጎ ሾመን።
እናንተም ቀድሞ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ ነበር፤ በአሳባችሁና በክፉ ሥራችሁም ምክንያት ጠላቶች ነበራችሁ። አሁን ግን ቅዱሳንና ንጹሓን፤ ነቀፋም የሌለባችሁ አድርጎ በፊቱ ሊያቀርባችሁ በልጁ ሞት እግዚአብሔር ከራሱ ጋር አስታረቃችሁ። ይህም በእርሱ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ
ይህንንም ያደረገው በመስቀሉ አማካይነት በመካከላቸው የነበረውን ጠላትነት ገድሎ ሁለቱን ሕዝቦች አንድ አካል በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ነው።
ከራሱ ጋር ያስታርቅ ዘንድ ስለ ወደደ ነው። እግዚአብሔር ልጁ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም በሰማያትም ሆነ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስታረቀ።
ስለዚህም እግዚአብሔር በእኛ ሆኖ ልመናውን እንደሚያቀርብ፥ የክርስቶስ ተወካዮች ሆነን ተሹመናል። ከእናንተም ጋር በመሆን ስለ ክርስቶስ "ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ!" ብለን ልመና እናቀርባለን።
ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን ይህንን ዕርቅ ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እኛ ደግሞ በእግዚአብሔር ደስ ይለናል።
ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር ርቃችሁ የነበራችሁት በክርስቶስ ኢየሱስ በመሆን በክርስቶስ ደም አማካይነት ወደ እግዚአብሔር እንድትቀርቡ ተደርጋችኋል።
በእምነት ስለ ጸደቅን በጌታችን በኢየሱስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን።