ስለ መስቀል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ መስቀል የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 1ኛ ቆሮንቶስ 1:18

ስለመስቀሉ ያለው መልእክት ለሚጠፉት ሞኝነት፤ ነገር ግን ለምንድን ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው።

02 ገላቲያ 6:14

ዓለም ለእኔ ከተሰቀለበት እኔም ለዓለም ከተሰቀልኩበት ከክርስቶስ መስቀል በስተቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።

03 ቆላስይስ 2:14

እርሱ ይከሰን የነበረውን የዕዳ ጽሑፍ ደመሰሰው። ሁሉንም በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከእኛ አስወገደው።

04 ፊልጵስዩስ 2:8

እንዲሁም እስከ ሞት፤ያውም እስከ መስቀል ሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።

05 1ኛ ጴጥሮስ 2:24

ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።

06 ዕብራዊያን 12:2

በእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ ኢየሱስ ላይ ዓይኖቻችን እንትከል። እርሱ ከፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉንና መስቀሉ የሚያስከትለውን ውርደት ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።

07 ዮሐንስ 12:32

እኔ ከምድር ከፍ ከፍ በምልበት ጊዜ፣ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ።»

08 1ኛ ቆሮንቶስ 2:2

በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀርና፥ እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ እንዳላውቅ ወስኜ ነበርና።

09 ገላቲያ 5:11

ወንድሞች ሆይ እስከአሁን ተገረዙ እያልኩ የምሰብክ ቢሆን ለምን እሰደድ ነበር? እንግዲያውስ የመስቀሉ እንቅፋት ይደመሰሳል።

10 ኤፌሶን 2:16

ይህንንም ያደረገው በመስቀሉ አማካይነት በመካከላቸው የነበረውን ጠላትነት ገድሎ ሁለቱን ሕዝቦች አንድ አካል በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ነው።

11 ቆላስይስ 1:20

ከራሱ ጋር ያስታርቅ ዘንድ ስለ ወደደ ነው። እግዚአብሔር ልጁ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም በሰማያትም ሆነ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስታረቀ።

ተዛማጅ ርዕሶች