ስለ መሥዋዕት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ መሥዋዕት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዕብራዊያን 9:14

ይልቁንም ነውር ሳይኖረው በዘላለማዊ መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናገለግል ዘንድ ሕሊናችንን ከሞተ ሥራ ምን ያህል ያነጻን ይሆን?

02 ዕብራዊያን 10:10

በሁለተኛው ሥርዓት ለአንድ ጊዜና ለዘላለም በቀረበው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ አማካኝነት በእግዚአብሔር ፈቃድ ተቀድሰናል።

03 ኤፌሶን 5:2

እንደ ወደደን፥ ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንዳቀረበ ሁሉ እናንተም በፍቅር ኑሩ።

04 ዕብራዊያን 9:28

እንደዚሁም የብዙዎችን ኃጢአት ለማስወገድ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው ክርስቶስ ኃጢአትን ለማስወገድ ዓላማ ሳይሆን በትዕግሥት ለሚጠባበቁት ድነትን ያስገኝላቸው ዘንድ ዳግመኛ ይገለጣል

05 1ኛ ዬሐንስ 2:2

እርሱ የእኛ ብቻ ሳይሆን፣ የዓለሙም ሁሉ ሃጢዓት ማስተስረያ ነው፣፡፡

06 ዕብራዊያን 7:27

እርሱ ሊቀ ካህናቱ ሲያደርጉት እንደነበረው በመጀመሪያ ራሱ ለሠራቸው ኃጢአቶች ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ለፈፀሟቸው ኃጢአቶች በየቀኑ መሥዋዕቶችን ማቅረብ አያስፈልገውም። ራሱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ይህንን ለአብዴና ለመጨረሻ ጊዜ አድርጎታል።

07 ዕብራዊያን 9:26

እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ከዓለም ጅማሬ አንስቶ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር። አሁን ግን ራሱን መሥዋዕት በማድረግ ኃጢአትን ለማስወገድ በዘመናት መጨረሻ የተገለጠው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

08 ሮሜ 3:25

በደሙ በማመን የኃጢአት ማስተሰሪያ ይገኝ ዘንድ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ሰጥቷልና። በትዕግስቱ የቀደመውን ኃጢአት ስለመተዉ ለጽድቁ ማረጋገጫ እንዲሆን ክርስቶስን መስዋዕት አድርጎ

09 ዕብራዊያን 10:14

ይህም በአንድ መሥዋዕት የተቀደሱትን ለዘላለም ፍጹማን ስላደረጋቸው ነው።

10 ኢሳይያስ 53:10

እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፣ ዕድሜውም ይረዝማል፣ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።

11 ዕብራዊያን 10:12

ነገር ግን ክርስቶስ ለኃጢአት ሁሉ ለዘላለም የሚሆን አንድ መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ፣

12 ዮሐንስ 10:11

መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ለበጎቹ ሲል ነፍሱን ይሰጣል።

13 ዕብራዊያን 2:9

ይሁን እንጂ፣ ከመከራውና ከሞቱ የተነሣ ከመላእክቱ በጥቂቱ አንሶ የነበረውን ኢየሱስ፣ የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖለት እናያለን። በእግዚአብሔር ጸጋ እርሱ ለሰው ሁሉ ሞትን ቀምሷል።

14 ዕብራዊያን 13:12

ደግሞም ኢየሱስ ሰዎችን በገዛ ደሙ ለመቀደስ ከከተማይቱ ቅጥር ውጭ መከራን ተቀበለ።

ተዛማጅ ርዕሶች