ስለ ተፈጸመ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ተፈጸመ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዮሐንስ 19:30

ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከጠጣ በኋላ «ተፈጸመ» አለ። ራሱንም አዘንብሎ ሞተ።

02 ዕብራዊያን 10:12

ነገር ግን ክርስቶስ ለኃጢአት ሁሉ ለዘላለም የሚሆን አንድ መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ፣

03 ዕብራዊያን 9:12

ክርስቶስ እጅግ ቅድስት ወደሆነችው ስፍራ አንድ ጊዜ ለሰዎች ሁሉ የገባውና የዘላለም ቤዛችንን ያስገኘልን በፍየሎችና በጥጃዎች ደም ሳይሆን በራሱ ደም ነው።

04 ቆላስይስ 2:14

እርሱ ይከሰን የነበረውን የዕዳ ጽሑፍ ደመሰሰው። ሁሉንም በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከእኛ አስወገደው።

05 ሮሜ 8:1

ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም።

06 ዕብራዊያን 10:14

ይህም በአንድ መሥዋዕት የተቀደሱትን ለዘላለም ፍጹማን ስላደረጋቸው ነው።

07 ዮሐንስ 17:4

አባት ሆይ፣ እንዳከናውነው የሰጠኸኝን ሥራ በመፈጸም በምድር ላይ አከበርሁህ፡፡

08 ዕብራዊያን 1:3

ልጁ የክብሩ ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም አንድ ነው፤ በሥልጣን ቃል ሁሉን ደግፎ ይዞአል። የሰዎችንም ኃጢአት ካነዳ በኃላ በሰማይ በግርማው ቀኝ ተቀምጧል።

09 ዕብራዊያን 7:27

እርሱ ሊቀ ካህናቱ ሲያደርጉት እንደነበረው በመጀመሪያ ራሱ ለሠራቸው ኃጢአቶች ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ለፈፀሟቸው ኃጢአቶች በየቀኑ መሥዋዕቶችን ማቅረብ አያስፈልገውም። ራሱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ይህንን ለአብዴና ለመጨረሻ ጊዜ አድርጎታል።

10 ሮሜ 6:10

ስለኃጢአት የሞተው ሞት ለዘላለም የሚሠራ የአንድ ጊዜ ሞት ነው። ይሁንና የሚኖረውን ሕይወት ለእግዚአብሔር ይኖራል።

11 ዕብራዊያን 9:26

እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ከዓለም ጅማሬ አንስቶ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር። አሁን ግን ራሱን መሥዋዕት በማድረግ ኃጢአትን ለማስወገድ በዘመናት መጨረሻ የተገለጠው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

12 ዮሐንስ 19:28

ኢየሱስ ሁሉ እንደ ተፈጸመ ዐውቆ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈው እንዲፈጸም፣ «ተጠማሁ» አለ።

13 1ኛ ጴጥሮስ 3:18

እንዲሁም ክርስቶስ አንድ ጊዜ ስለ ኀጢአታችን ሞቷል። ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ፣ ጻድቅ የሆነው እርሱ ስለ እኛ ስለ ዐመፀኞች ሞተ፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤

ተዛማጅ ርዕሶች