ስለ በሐቀኝነት የተገኘ ትርፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ በሐቀኝነት የተገኘ ትርፍ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ምሳሌ 13:11

ብዙ ከንቱነት ሲኖር ሀብት እየመነመነ ያልቃል፣ በእጁ እየሰራ ገንዘብ የሚያከማች ሰው ግን ገንዘቡ እየጨመረ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡

02 ምሳሌ 16:8

ፍትህ በጎደለው መንገድ ከተገኘ በርካታ ገቢ ይልቅ፣ በጽድቅ የተገኘ ጥቂት ገቢ ይሻላል፡፡

03 ምሳሌ 20:23

እኩል ያልሆኑ ሚዛኖችን እግዚአብሔር ይጠላል፣ ሐሰተኛ መስፈሪያም መልካም አይደለም፡፡

ርዝመትን፣ ክብደትን፣ ወይም ብዛትን ስትለኩ፡፡ ሀሰተኛ መለኪያ አትጠቀሙ፡፡ ትክክለኛ መስፈሪያን፣ ትክክለኛ ሚዛኖችን፣ ትክክለኛ የኢፍ እና የኢን መለኪያዎችን ተጠቀሙ፡፡ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡

05 ምሳሌ 28:6

በመንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይልቅ፣ በሐቀኝነቱ የሚራመድ ድሃ ሰው ይሻላል፡፡

06 ምሳሌ 11:1

እግዚአብሔር ትክክለኛ ያልሆነ ሚዛን ይጠላል፣ በትክክለኛ ሚዝን ግን ሚዛን ደስ ይለዋል፡፡

07 ምሳሌ 10:2

በክፋት የተከማቸ ሃብት ምንም ጥቅም የለውም፣ ጽድቅ ግን ከሞት ያድናል፡፡

08 ኤርሚያስ 17:11

ያልጣለችውን እንቁላል እንደምታቅፍ ቆቅ፣ እንዲሁ አንድ ሰው ያለፍትህ ባለጠጋ ይሆን ይሆናል። ነገር ግን በእኩሌታ ዘመኑ ላይ ብልጥግናው ይተወዋል፣ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።

ጎረቤትህን አትበድል ወይም አትዝረፈው፡፡ የቀን ሰራተኛውን ክፍያ በአንተ ዘንድ አታሳድር፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች