ስለ እግዚአብሔር ቀላቢያችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ እግዚአብሔር ቀላቢያችን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ደግሞም አምላኬ እንደ ክብሩ ባለጠግነቱ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል።
ነገር ግን በመጀመሪያ መንግሥቱንና ጽድቁን ፈልጉ፤ ከዚያም እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል፡፡
ያህዌ እረኛዬ ነው፤ ምንም አላጣም፡፡
አብርሃምም ያን ቦታ «እግዚአብሔር ያዘጋጃል» ብሎ ጠራው። ዛሬም ቢሆን ሠዎች «እግዚአብሔር በተራራው ላይ ያዘጋጃል» ይላሉ።
አንበሶች ሊያጡ ሊራቡም ይችላሉ ያህዌን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጐድልባቸውም፡፡
እግኢአብሔር ሁልጎዜ በነገር ሁሉ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝቷችሁ በብጎ ስራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።
የማይዘሩትን ወይም የማያጭዱትን ቁራዎችን ተመልከቱ። መጋዘን ወይም ጐተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል። ከወፎች ይልቅ እናንተ ምን ያህል የላቀ ግምት ያላችሁ ናችሁ?
የሁሉም ዐይን አንተን በተስፋ ይጠብቃል በተገቢ ጊዜ ምግባቸውን ትሰጣቸዋለህ፡፡ እጅህን ትዘረጋለህ የሕያዋንን ሁሉ ፍላጐት ታረካለህ፡፡
አምላካችን ያህዌ ፀሐይና ጋሻችን ነውና፤ ያህዌ ጸጋንና ክብርን ይሰጣል፤ በቅንነት የሚሄዱትን መልካም ነገር አይነፍጋቸውም፡፡
እንግዲህ፥ እናንተ ክፉዎች የሆናችሁ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ የሚኖር አባታችሁ ለሚለምኑት አብዝቶ መልካም ስጦታን እንዴት አይስጣቸውም?