ስለ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ቆላስይስ 2:9

የእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት በእርሱ ይኖራልና።

02 ዮሐንስ 1:14

ቃል ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋና እውነት የተሞላውን ከአብ ዘንድ ያለውን የአንድያ ልጁን ክብር አየን፡፡

03 ዕብራዊያን 2:17

ስለሆነም የእግዚአብሔር በሆነ ነገር ሁሉ መሓሪና ታማኝ ሊቀ ካህን ለመሆንና ለሰዎችም ሁሉ የኃጢአት ይቅርታን ለማስግገኘት በሁሉም ረገድ ወንድሞችን መምሰሉ አስፈላጊ ሆነ።

04 1 ጢሞቴዎስ 2:5

አንድ እግዚአብሔር አለና፣ እንዲሁም በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል፣ ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ አንድ መካከለኛ አለ፤

05 ዕብራዊያን 4:15

ነገር ግን እርሱ ከኃጢአት በቀር በማንኛውም ነገር እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንምና።

06 ዮሐንስ 1:1

በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፤

07 ሮሜ 9:5

ከሁሉ በላይና ለዘላለም የእግዚአብሔር ብሩክ የሆነው ክርስቶስ በሥጋ የመጣው ከአባቶቻቸው ነው። ለእርሱ ለዘላለም ምስጋና ይሁን። አሜን!

08 ቲቶ 2:13

ይህም የተባረከውን ተስፋችንን፣ የታላቁን አምላካችንና አዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ፣ ለመቀበል በደስታ እንድንጠባበቅ ነው።

09 ዮሐንስ 20:28

ቶማስም፣ «ጌታዬና አምላኬ» ብሎ መለሰለት።

10 ዕብራዊያን 1:8

ስለ ልጁ ግን፣ “አምላክ ሆይ፣ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ነው፤ የመንግሥትህም በትር የጽድቅ በትር ነው።

11 ፊልጵስዩስ 2:6-7

እርሱም የመለኮት ባሕር ነበረው፥ ነገር ግን ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሚያደርጋውን የመለኮት ባሕይ እንደ ያዘ አልቆጠረም። ክብሩን ትቶ ራሱን ባዶ አደረገ። የባሪያንም መልክ ያዘ፤ በሰው አምሳል ተገለጠ፤ እንደ ሰውም ሆኖ በትህትና ራሱን ዝቅ አደረገ።

ተዛማጅ ርዕሶች