ስለ ወልደ እግዚአብሔር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ወልደ እግዚአብሔር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዮሐንስ 20:31

ነገር ግን ይህ የተጻፈው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ እንድታምኑና አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንድታገኙ ነው።

02 የማቴዎስ 3:17

እነሆ፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው። "በእርሱ እጅግ ደስ ይለኛል" የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።

03 የማቴዎስ 16:16

ስምዖን ጴጥሮስ፣ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" በማለት መልስ ሰጠ፡፡

04 ሮሜ 1:4

እርሱም በቅድስና መንፈስ ኃይል ከሙታን በመነሳት የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ የተነገረለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር።

05 1ኛ ዬሐንስ 5:11-12

ምስክሩም ይህ ነው ፣እግዚአብሔር የዘላለምን ህይወት እንደሰጥንና፣ይህም ህይወት በልጁ መሆኑ ነው። ልጁ ያለው ሕይወት አለው፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።

06 ዕብራዊያን 1:5

ለመሆኑ፣ ከመላክት መካከል፣ “አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ደግሞስ፣ “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ለማን ነው?

07 ዮሐንስ 3:16

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፤

08 ማርቆስ 1:1

ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፡፡

09 ሉቃስ 1:35

መልአኩም እንደዚህ በማለት መለሰላት፣ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፣ የልዑል ኃይልም በአንቺ ላይ ያርፋል፤ ከዚህ የተነሣም የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡

10 ዮሐንስ 5:25

እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእኔን፣ የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ አሁንም መጥቶአል፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።

11 ገላቲያ 2:20

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።

12 ዮሐንስ 10:36

እኔ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ስላልሁ፣ አብ ቀድሶ ወደ ዓለም የላከውን እንዴት የስድብ ቃል ሰነዘረ ትሉታላችሁ?

ተዛማጅ ርዕሶች