ስለ የፍጥረት ሁሉ በኩር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የፍጥረት ሁሉ በኩር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ቆላስይስ 1:16

ምክንያቱም በሰማያትና በምድር፤ የሚታዩትና የማይታዩት ነገሮች ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል። ዙፋናትም ሆኑ ኅይላት ወይም ግዛቶችች ወይም ሥልጣናት፤ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥረዋል።

02 ቆላስይስ 1:17

እርሱ ከሁሉ በፊት ነበረ፤ሁሉም ነገር የተያያዘው በእርሱ ነው።

03 ዮሐንስ 1:3

ሁሉም ነገር የተሠራው በእርሱ አማካይነት ነው፤ ከተሠሩት ነገሮች ሁሉ ያለ እርሱ የተሠራ አንድም ነገር አልነበረም፡፡

እንዲሁም ታማኝ ምስክር፥ከሙታን በኩርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለሚወደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፥

05 ዕብራዊያን 1:6

የበኩር ልጁን ወደ ዓለም ሲያስገባ እግዚአብሔር፣ “የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ብሏል።

06 ዕብራዊያን 1:2

አሁን ግን የሁሉም ነገር ወራሽ ባደረገው፣ ዓለምንም በፈጠረበት በልጁ ተናገረን።

07 1ኛ ቆሮንቶስ 8:6

እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ ብቻ አለን፤ እንዲሁም ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አለን።

08 ቆላስይስ 1:18

እርሱ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱ የሁሉም መገኛና የሁሉም የመጀመሪያ፣ከሙታንም በኩር ነው።

09 ሮሜ 8:29

ምክንያቱም አስቀድሞ ያወቃቸውን እነርሱን በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወሰነ።

10 ዮሐንስ 1:10

እርሱ በዓለም ውስጥ ነበር፤ ዓለሙም የተሠራው በእርሱ ነው፤ ዓለም ግን አላወቀውም፤

ተዛማጅ ርዕሶች